አፈናቃይ፣ነቃይ እና ተካዩ የኦነግ/ኦዴፓ ፅንፈኛ መንግስት ተረኛ ያደረጋቸው የአዲስ አበባ ፍል ውሀ ነዋሪዎች!
ማፈናቀል፤መንቀል እና መትከልን ስራዬ ብሎ የተያያዘው ፅንፈኛው #የኦነግ/ኦዴፓ መንግስት ቤታቸውን ያፈረሰባቸው የፍልውሀ ነዋሪዎች ያቀረቡትን የሰቆቃ ጥሪ ተከትሎ ተፈናቃዮችን ለመጠየቅ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በስፍራው ቢገኝም ፖሊስ ተፈናቃዮችን እንዳያናግር ክልከላ እንዳደረገበት ገለፀ ።
"ፍልዉሃ ፖስታ ቤት ጀርባ ከትላንት ለሊት ጀምሮ ቤታቸው የፈረሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪን ለመጠየቅ ባልደራስ በስፍራው ቢገኝም ፖሊስ ተፈናቃዮችን እንዳናናግር ከለከለ።
ሚያዚያ 29/2012 ዓም ትላንት ምሽት ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፖስታ ቤት ጀርባ ቤታቸው የፈረሰባቸውን ዜጎች ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ በአካባቢዉ ነዋሪ የድረሱልን ጥሪ መሰረት በስፍራው ተገኝቶ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ በፖሊስ ክልከላ ምክንያት ጥየቃችን ሳንጨርስ ለመመለስ ተገደናል።
የባልደራስ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ በቦታው ተገኝቶ ተፈናቃዮችን ለማነጋገር ሲሞክሩ ፖሊስ በኃይል ጣልቃ በመግባት ዜጎች ችግራቸውን እንዳያስረዱ አድርጓል።
ፖስታ ቤት ጀርባ በአሁኑ ሰዓት በርከት ያሉ ተፈናቃይ ህፃናት እናቶችና አረጋውያን በቅርብ እርቀት ለአደጋ እንደተጋለጡ የታዘብን ሲሆን እቃቸውም ሜዳ ላይ እንደወቀ ለመታዘብ ተችሏል።
መንግስት በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚያካሄደውን ህገወጥ የዜጎች ማፈናቀል እንዲያቆም በተደጋጋሚ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ቢጠይቅም መንግስት የህዝብን ጥያቄ ችላ ብሎ በህገወጥ ጭካኔ በተሞላበት እብሪት ተግባሩን ቀጥሎበታል።
በዚህ ወረርሽኝ የኮሮና ቫይረስ በተለይ በታላቁ ረመዳን ፆም ወቅት አረጋዊያን እናቶች ማስጨነቅ ከመንግስት የማይጠበቅ ኃላፊነት የማይሰማዉ እኩይ ድርጊት መሆኑን ታዘብናል።
በነበረው ትንሽ ክፍተት ከሁለት እናቶች ጋር የተደረገ ልብ የሚሰብር ቃለ መጠይቅ ከ11:00 ሰዓት በኃላ እንለቀዋለን።
አዲስ አበባ - ባልደራስ
አዲስ አበባ - ባልደራስ
Comments
Post a Comment