"ለባልደራስ መረጃ ለምን ሰጣችሁ ተብለን በአስተዳደሩ አመራሮች እያስጨነቁን ይገኛል።
/የአዲስ አበባ ወጣቶች/
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ተጨማሪ ቋንቋ አትችሉም በማለት የደረሰብን በደል ለህዝብ ስናሳውቅ ዛቻና ማስፈራሪያ በተደራጁ ሃይሎች እየደረሰብን ነው ሲሉ አመልካቾች ለባልደራስ በድጋሚ ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ያወጣውን የስራ ቅጥር ምዘና ከሚገባው ወጤት በላይ በማስመዝገብ ለስራ ቅጥር ዝግጁ ቢሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በሰራው አሻጥር በመጀመሪያው ዙር ሳይቀጠሩ መቅረታቸው ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ወጣት አመልካቾች ለሰው ሃብት ልማት ቢሮው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተፈፀመው ድርጊት ስህተት መሆኑን ተቀብሎ በአንድ ወር ውስጥ እንደሚያርምና ቅጥር እንደሚፈፅምላቸው ቃል የገባ ቢሆንም ቃሉን ሳያከብር አራት ወራት ማለፉን አመልካቾች ለባልደራስ መግለፃቸው ይታወሳል።
በተደጋጋሚ ወደ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በቁጥር በርከት ያሉ አመልካቾች በማቅናት የገባውን ቃል እንዲያከብር ቢጠይቁም ተጨማሪ ቋንቋ አትችሉም በማለት መልስ ሳያገኙ ቀርተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የሚሰራዉን ዘረኝነት ሚያዚያ 26 2012 ዓም በባልደራስ ፅ/ቤት ተገኝተው ቅሬታ ማቅረባቸው የሚታወቅ ነው።
ይሁን እንጅ የአስተዳደሩ የሰው ሃብት ልማት ቢሮው ችግሩን መቅረፍ ሲገባው ለምን መረጃ ለባልደራስ ሰጣችሁ በሚል በአመልካቾች ተወክለው በመጡ ወጣቶች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እያደረሰባቸው ነው በድጋሚ ገልፀዋል።

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes