የአቶ ስብሐት ነጋ እብደት ምነው ሕክምና ተነፈገው?
አቶ ስብሐት ነጋ አንጋፋ የወያኔ መስራች ከመሆናቸውም በላይ የኢትዩጵያን ታሪክ የማጥፋቱን ፣የዘር ማፅዳቱን እና የድርጅታቸዉን የከፋፍለህ ግዛ ሰይጣናዊ ፖሊሲ በማስፈፀሙ ረገድ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ከቀን እንደሚደክሙ ይታወቃል።
ታዲያ አቶ ስብሐትን የመሰለ የዲያቢሎስ ስራ አስፈፃሚ ፣የወያኔ ቀንደኛ መስራች በአእምሮ በሽታ እየተሰቃዩ ድርጅታቸው ለሳቸው መላ ሳይፈልግ ፤ አንድ ቀንም በስልጣናቸው ሳይጠቀሙ ኖረው ቦታውን ለለቀቁት ለቀድሞው የኢትዩዽያ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ይሄን ያህል ጭንቅ ጥብብ ብሎት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ አዉጥቶ፤ ሊፍት አሰርቶ የወር ክፍያዉ 400000 ብር የሆነ ቤት አንጀቱን እስር አርጎ ለመከራየት ሲወስን አቶ ስብሐትን ግን ችላ ብሎ እያለፈ ነው።
እንዴ ወያኔ ምን ነካው?
ኧረ ወያኔ ምን ነካው ሰውየው እኮ ታመዋል። አምና ድርጅታቸው የሰራውን ዘንድሮ ከረሱ፣ወያኔ የተመሰረተበትን አማራንና ኦርቶዶክስን የማጥፋት ዋና አላማ "እቅዳችን ግቡን መቶአል የአማራንና የኦርቶዶክሱን ቀንድ ሰብረናል" ብለው ከተናገሩ በሑዋላ መልሰው ቃለ መጠይቅ ሲቀርብላቸው "ኧረ እኔ አላልኩም፤ብልም እንኩዋን ኧረ ወንድማችን ታሙዋል ብለው ሐኪም ቤት ይወስዱኛል እንጅ አይቀየሙኝም" ብለው አንጀታችንን ሲበሉ ከርመው ነበር።
አሁን ደግሞ አሜሪካንን የመሰለ ትልቅ ዲሞክራሲአዊ ሐገር ድረስ ሄደው ወያኔን ለማሰደብ ቦቅስ ለመቧቀስ ሲሞክሩ በአደባባይ እብደቱ ለየላቸው እንዴ? አስብሎአል። ያ ባይሆን ኖሮ የቤት ገበና እቤት ይቀር ነበር!!
ኧረ እናንተየ እውነቴን እኮ ነው፤ ሰውየው ታመዋል አታዩዋቸውም እንዴ ደረጀ ለሚጠይቃቸው ጥያቄ ሁሉ ሲዘባርቁ። ከዚህ በፊት እውቅና ሰጥተው የሾሙዋቸውን ሰላሳ ሶስት ጄኔራሎች ሁሉ መሾማቸውን "አላውቅም" ብለው እርፍ።
አይ እዉቀት መና! ደረጄ ሁለተኛ ግን እንዳይለመድህ ሰውየው ችግር እንዳለባቸው እያወቅክ አለርጅክ የሆነ ጥያቄ ትጠይቃቸዋለህ እንዴ?
እኔ ግን አቶ ስብሐትን ብሆን ድርጅቴ ለጤናየ ግድ የማይሰጠው ከሆነ ገና ድሮ ለቅቄ ወደ አምላኬ እቀርብ ነበር።
ለማንኛውም ቸር ይግጠመን ከየሺሀረግ በቀለ

Comments
Post a Comment