የባሕር ዳር ኗሪዎች ስንታየሁ ቸኮልን እንዳይጠይቁ ተከለከሉ !

# # ከታገቱ 48 ሰዓት ቢያልፋቸውም ፍ/ቤት አልቀረቡም!

/ በባሕር ዳር ከተማ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ በአደራ እስረኝነት በግፍ ታግተው የሚኙት ስንታየሁ ቸኮል በወዳጅና ዘመዶቻቸው ብሎም በመላው የባሕር ዳር ኗሪዎች እንዳይጠየቁ ተከልክሏል። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊ የሆኑት አቶ ስንታየሁ፣ ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከታፈኑ ጀምሮ ዛሬ ከ48 ሰዓት በላይ የሆናቸው ሲሆን፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። ይባስ ብሎ የባሕር ዳር ከተማ ኗሪዎች በፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው እንዳይጠይቋቸው ተከልክሏል። በዚህም ምክንያት ምግብ እየገባላቸው አይደለም። ትዕዛዙ ከበላይ አካል መምጣቱም ተጠቁሟል። በተጨማሪም ጥቃት ሊያደርሱባቸው እንደሚችሉ የፖሊስ ሓላፊዎች እየዛቱባቸው መሆኑን የፖሊስ ጣቢያው የውስጥ ምንጮች አረጋግጠዋል። እስር ቤቱ ባሕር ዳር ውስጥ ካሉት ሁሉ በመጥፎነቱ የሚታወቅ ነው። / #ኢትዮጵያ

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes