111 ሚዲያዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ ፖሊስ ፍንጭ ሰጠ!!

 

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ 111 የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን በሕገ ወጥነት ፈርጆ ለመዝጋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዛሬ ባወጣው ፍንጭ ሰጥቷል። ይህ ፍንጭ የተገኘው ፖሊስ ዛሬ ረቡዕ፤ ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም . ባወጣው መግለጫ ነው። መግለጫው መገናኛ ብዙሃኑን በስም ከመግለፅ የተቆጠበ ሲሆን፣ የመገናኛ ብዙሃን የስርጭት ፈቃድ ያልተሰጣቸው መሆኑን ጠቅሷል። እነኝህ መገናኛ ብዙሃን "ሕዝብን ከመንግሥት ለመነጠል ይሠራሉ" ሲልም እሮሮውን አሰምቷል። በዚሁ ምክንያት ፖሊስ 10 ጋዜጠኞችን አስሮ እያንገላታ መሆኑን አምኗል። በተግባር የታሰሩት ግን 19 ናቸው። በፕሬስ ነፃነት አዋጅ መሰረት ማንኛውም ጋዜጠኛ በሥራው ምክንያት ቢከሰስ እንኳን፤ ዶሴውን በውጭ ሆኖ መከታተልና መከራከር እንጂ በእስር ቤት እንዲቆይ አይገደድም። ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ / #ኢትዮጵያ

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes