የአማራ ልዩ ኃይል አባላት፣ "ዘመነ እንዳይገኝ መረጃ እያወጣችሁ ነው" ተብለው እየተወነጀሉ ናቸው!!

 መረጃ

# የመንግስት ታጣቂዎች የሜጫን አካባቢ እያዋከቡ ነው ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ!! / የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) መሪ ዘመነ ካሴን ፍለጋ የገባው የመከላከያ ኃይል፣ ከአዴት ዴንሳ ባታ እስከ ብራቃት ያለውን መንገድ ወጥሮ ሕዝቡን እያዋከበ መሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። በጎጃም መራዊ አካባቢ የተሰማራው የመንግስት ታጣቂ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት ዘግቶ አርሶአደሩ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ ደንቃራ እስከመሆን ደርሷል። በዚህም ሳቢያ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እንደ ልብ ተንቀሳቅሶ የዕለት ከዕለት ስራውን ማከናወን አለመቻሉን ነው የአካባቢው ኗሪዎች የሚገልፁት። በህግ ማስከበር ሽፋን ሰላማዊ ህዝብን ማሸበር ባስቸኳይ ሊያቆም ይገባል ብለዋል። በሌላ በኩል፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት፣ "ዘመነን እንዳናገኝ መረጃ እያወጣችሁ ነው" ተብለው እየተወነጀሉ መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ናቸው። ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ / #ኢትዮጵያ

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes