Ethiopia:-ከፍልውሃ -ኮዬፈጬ

ከፍልውሃ -ኮዬፈጬ
.."ከፍልዉሃ ፖስታ ቤት የተፈናቀሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ኮዬፈጬ መብራትና ውሃ በለሌው አካባቢ እንዲቀመጡ ተደርጓል።
በባልደራስ ተጽኖ በህዝብ ግፊት ተፈናቃይ ድሆች ወደ ኮዬፈጬ ቢወሰዱም ውሃና መብራት በሌለበት አስቸጋሪ ስፍራ እንዲቀመጡ አድርገዋል። ለባልደራስ ቤታችን ፈረሰ ብላችሁ ለምን መረጃ ሰጣችሁ በማለች ዛቻና ማስፈራራትም እየደረሰብን ይገኛል ብለዋል።
ህገወጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየጊዜዉ የሚያፈናቀላቸው ወገኖች እለት በእለት ባልደራስ እየተከታተለ ለህዝብ በማድረሱ ከፍተኛ ውግዘት ህዝባዊ ተቃዉሞ ሲያስተናግድ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ድርጊቱን በመግለጫ እንዳወገዙት ይታወቃል። ከፍልዉሃ ፖስታ ቤት የተነሱ አዲስ አበቤዎች ለ33 አባዎራ ኮዬፈጬ በጊዚያዊነት ቦታ ቢሰጣቸውም አሁንም በችግር ላይ እንዳሉ ከደረሰን መረጃ ማረጋገጥ ችለናል።

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes