(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ለማስታወስ በማህበራዊ ሚዲያዎች ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ታወቀ። በቲውተርና በፌስቡክ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ዘመቻ በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ሆነዋል። በየእስር ቤቱ በስቃይ ላይ የሚገኙትንና በግፍ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ፎቶግራፎች በመለጠፍና ስቃያቸውን በመዘርዘር ትኩረት እንዲያገኝ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። ዘመቻውን የሚያስተባብሩት በኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግለሰቦች እንደሆኑም ታውቋል። ዛሬ ፌስቡኩ በኢትዮጵያውያን አንድ ዘመቻ ተወሯል። መልዕክቱ ተመሳሳይ ሆኖ በዓለም ዙሪያ ባሉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲስተጋባም ውሏል። የዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የአቶ ኦኬሎ አኳይ፣ የወጣት ንግስት ይርጋ፣ የወጣት ሴና ሰለሞን፣ የአቶ በቀለ ገርባ፣ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የብ/ጄነራል ተፈራ ማሞና የሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች ፎቶግራፎች እየተለጠፉ በመታወስ ላይ ናቸው። ባለፉት 26 ዓመታት በህወሀት አገዛዝ በግፍ የተሰቃዩ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት የደረሰባቸው፣ ወደ እስር ቤት በህይወት ገብተው በሞት የወጡ አያሌ ኢትዮጵያውያን ዛሬ እየታወሱ የዋሉበት ቀን ነው ። የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ በኦነግ ስም የታሰሩ፣ በኦብነግ ተጠርጠረው የገቡ፣ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናችሁ ተብለው የሚሰቃዩና ሌሎችም በስም ተዘርዝረው የደረሰባቸው ስቃይና መከራ ተገልጾ እንዲታወሱ ተደርገዋል። በምርመራ ወቅት የእግርና የእጅ ጥፍሮቻቸው የተነቀሉባቸው፣ በብልታቸው ላይ የታሸገ ውሃ እንዲንጠለጠል የተደረገባቸው፣ በኤሌክትሪክ ሽቦ ሰውነታቸው እስኪተለተል የተገረፉና የተቃጠሉ፣ በማንነታቸው የተዘለፉና የስነልቦና ጉዳት የደረሰባቸው በፎቶግራፍና በስም እየተጠቀሱ የታወሱበት ቀን ነው። በአዲስ አበባ በግል የሚንቀሳቀሱ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተቆርቆሪዎች ያስጀመሩት ዘመቻ በተለይም በቲውተርና በፌስ ቡክ በሰፊው በመካሄድ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የዘመቻው አንዱ አስተባባሪ የሆነው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በቂሊንጦ እስር ቤት ተነስቶ በነበረው ቃጠሎ ምክንያት በግፍ የተገደሉ የ15 እስረኞችን ፎቶግራፎች በማውጣት እንዲታወሱ አድርጓል። ሌላው የዘመቻው አስተባባሪ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉም በእስር ቤት ህይወታቸው ያለፉ ኢትዮጵያውያንን የጥቂቶቹን በስም በመዘርዘር እንዲዘከሩ ማደረጉን ለማወቅ ተችሏል። በዚህም ኢንጅነር ተስፋሁን ጨመዳ ፣ ኒሞና ጥላሁን፣ ሙባረክ ይመር፣አየለ በየነ፣ አብደታ ኦላንሳ፣አርማዬ ዋቄ ማሞና መሐመድ ጫኔ በእስር ቤት በደረሰባቸው ድብደባና ስቃይ ምክንያት ህይወታቸውን ካጡት መሃል በስም ተጠቅሰው ተዘክረዋል። ዘመቻው ሁሌም እናስታውሳችኋለን በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ነው። የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የሆኑት ኢትዮጵያውያኑ ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው፣ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ያወጣውን ህገመንግስት ተቀብለው መብታቸውን በመግለጻቸው፣ እንደወንጀለኛ ተቆጥረው ለዓመታት በማጎሪያ እስር ቤቶች መሰቃየታቸውን፣ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሰቆቃ፣ግርፋትና ድብደባ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑን ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ያለመው የዛሬው ዘመቻ የብዙዎችን ትኩረት አግኝቷል። በዛሬው ዘመቻ በህወሀት መንግስት ለተቋቋመው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ግልጽ ደብዳቤ ተዘጋጅቶ እንዲደርሰው የተደረገ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
Prof. Berhanu Nega’s Address to the European Parliament – Full Text Ethiopia as an Anchor for Peace and Stability in the Horn of Africa and The Need for a Broad-based Transitional Political Order By Berhanu Nega Dec 2 2015 Honorable chair, and distinguished members of the European parliament Ladies and Gentlemen: Allow me to first express my sincere condolences to the families of the victims, to the People of France and the European Community in general for the most recent senseless and barbaric terrorist crime committed against innocent people in Paris on the evening of November 6. In my view, such acts are not only contrary to the basic norms of civilized behavior and devoid of rudimentary moral principles, they can never be an acceptable instrument to achieve any objective, no matter how...
Comments
Post a Comment