የወደፊትዋ ኢትዮጵያ ጉባኤ 2017 አዘጋጅ ግብረ ሐይል መግለጫ
ETHIOPIA FUTURE CONFERENC -2017 PRESS RELEASE .
የሰብዓዊ መብት እና ፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረሐይል :-በሐገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኛው እና ፋሺስቱ ወያኔ በዜጎች ላይ የሚያደርሰውን መጠን የለሽ እስር፣ግድያ፣የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሐገር የማፍረስ ተልዕኮ በመቃወም በተለያዬ መልክ ፍትሕ፣እኩልነት እና ነፃነት የሰፈነባትን የጋራ ሐገር ለመመስረት በመላው የአውሮፓ ሐገሮች በተለያዬ መልክ ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አክቲቪስቶች የመሰረቱት ግብረ ሐይል ሲሆን ከተቁዋቁዋመበት ጊዜ አንስቶ ትላልቅ አውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፎችን በመጥራትም ሆነ ሌሎች የተለያዩ ነገሮችን በማድረግ የወያኔን አፓርታይድ ስርዓት እኩይ ተግባር ሲያወግዝ እና ለታፈነው ሕዝብ ድምፅ ሲሆን የቆየ ሲሆን :-
አሁን ደግም ከምንጊዜውም በላይ ፋሺስቱ ወያኔ በረጨው የከፋፍለህ ግዛ የመርዝ ፖለቲካ ምክንያት ሐገሪቱን እና ሕዝቡዋን ውጥንቅጡ ለወጣ እልም ያለ የማሕበራዊ ኑሮ እና የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መክተቱ አልበቃ ብሎት ከመቀሌ አዲስ አበባ ፣ከአዲስ አበባ መቀሌ እያለ ከቻለ ሕዝቡን እርስ በርስ እያጫረሰ እረግጦ ሊገዛ ካልቻለ ደግሞ ሐገሪቱን ብትንትኑዋን ሊያወጣ በሚችልበት ነገር ላይ መቀሌ ላይ ቤት ዘግቶ በሚመክርበት በዚህ ወቅት አለን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ምሁራኖች ፣ አክቲቪስቶች፣እና የሲቪክ ማህበራት በሙሉ ተሰባስበው በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ የሚያቀርቡበት እና ልዩነቶቻቸውን አስወግደው የሁሉም ዜጎች መብት የተረጋገጠባትን ምቹ የሆነች ኢትዮጵያ ልትመሰረት የምትችልበት የጋራ ጉዳይ ላይ የሚነጋገሩበት ትልቅ መድረክ መዘጋጀት አለበት ብሎ ስላመነ :-
ሰብአዊ መብት እና ፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረ፡ሐይል በአውሮፓ ከጀርመን ፍራንክ ፈርት ግብረ ሐይል ጋር በመተባበር ከስድስት ወር በላይ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየበት Ethiopia future የተሰኘው ጉባኤ ዲሴምበር 9 እና 10 /2017 ከ10 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
በመርሐ ግብሩ መሰረት በዲሴምበር 9 እና 10ቀን በሚካሄደው ጉባኤ ላይ በተለያዮ ትልልቅ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ ምሁራን እና አክቲቪስቶች የተዘጋጁ: -
-ጥናታዊ
ፅሁፎች ለምሳሌ
·Ethiopia political
reallity and hopes for future(Ms. Anna Gomes)
·The politics of Economics
growth in Ethiopia(Prof.Getachew Begashaw)
· Human rights situation in Ethiopia,(Yared Hailemariam)
·The role of the diaspora community and civic organisation
in the movement for change,(ato Abere Adamu)
·The challenges of building a united front for change,(ato.Geresu
Tufa)
·Has the west helped or hindered change in Ethiopia?,
·Visions for Ethiopia beyond EPRDF.
የተሰኙት ከሚቀርቡት ከብዙ በጥቂቱ ሲሆኑ ,
-ውይይት ይደረጋል፣
-የሚነሱ ጥያቄዎች ይስተናገዳሉ፤የሞተ አህያ ጅብ አይፈራም!!! የተሰኘው ፊልም ይታያል ።
ስለዚህ በመላው አውሮፓ
ያሉ ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኖችን ሁሉ የጉባኤው ታዳሚ ይሆኑ ዘንድ ግብረ ሐይሉ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል።
Date: Desember 9 and 10/2017,Time from 10:00-18:00
Pleace:-SaabauNiederrad Goldsteinsrasse , 33 60528, Frankfurth am main
Germany
ለበለጠ መረጃ https://www.facebook.com/groups/1518819844834395/
የፌስቡክ ገፃችንን ይመልከቱ !!!
ነፃነት ፣ፍትሕ ፣እኩልነት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ሰብአዊ መብት እና ፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረ፡ሐይል በአውሮፓ ከጀርመን ፍራንክ ፈርት ግብረ ሐይል ጋር በመተባበር
Comments
Post a Comment