ለግንቦት7 ህዝባዊ ሐይል የተደረገ የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም እና ስኬት

            የወያኔ አሸባሪ ግሩፕ እና ሆዳደር ደጋፊዎቹ እንቢ ነፃነቴን ብሎ የሚነሳዉን ንፁሐን ሕዝብ ሁሉ በአሸባሪነት መፈረጁ የተለመደ የዘወትር ተግባራቸው ነዉ ፤የሌባ አይነ ደረቅ እንዲሉ።በገዛ ሀገሩ ባይተዋርነቱ፣ጉስቁልናው፣እንግልቱ የሰለቸው ህዝብ መነሳሳት ያስፈራው የወያኔ መንግስት ፍፁም መጃጃል እየታየበት መጥቶአል።
   ይህን የምለው ያለምክንያት አይደለም፤ከደደቢት ተነስቶ ያላንዳች እውቀት ዕኩይ ተግባሩን ይዞ፣ የጠመንጃን አፈሙዝ ጉልበቱ በማድረግ22 ዓመት ስልጣን ላይ የተፈናጠጠዉ የወያኔ መንግስት ሕዝብ አንድ ቀን በቃኝ፣ሰለቸኝ እንደሚል አውቆ እራሱን ማስተካከል የነበረበት ሲሆን የወያኔው ተግባር ግን እጅግ በተቃራኒው ነው።
የራሱን አፋኝ የስለላ ተግባር በሀገር ውስጥ እና እዉጭ ባሉ ኢትዮዽያውያን ላይ ሆዳደር ሰላዮችን መልምሎ ማሰማራት።
    እናም ሰሞኑን የወገናቸው ጉስቁልና፣ ሰቆቃና የሀገራቸው የወደፊት እጣ ፈንታ ያሳሰባቸው ኢትዮዽያውያን በኖርዌ የግንቦት ፯ ህዝባዊ ሀይልን ለመደገፍ የሚያደርጉትን የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ለማደናቀፍ ከላይ እታች ሲሉ ከርመዋል። አልፈው ተርፈውም በተላላኪዎቻቸው በኩል አሸባሪን ለመርዳት እየተንቀሳቀሱ ነው በማለት እዚህ ዲሞክራሲ ያለበት ሀገር ውዠንብር ሲነዙ ቢከርሙም የኖርዌ ፕሮፌሰር በሀገሪቱ ውስጥ ለሚታተም አንድ ጋዜጣ እየረዳን ያለነው የግንቦት ፯ ሕዝባዊ ሀይል በየትኛዉም ዓለም በአሸባሪነት እንዳልተመዘገብ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
   የገንዘብ ማሰባሰቡም ተግባር የህዝባዊ ሀይሉ ከፍተኛ አመራር ኮማንደር አሰፋና የግንቦት 7 የፍትሕ ፣የነፃነትና ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ለዉጥ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳዊት መኮንን እና የተለያዩ  ኢትዮዽያውያን  የበኩላቸውን ለማበርከት በተገኙበት በታሰበበት ቀን መስከረም28/09/2013 ከመካሄዱም በላይ ውጤቱም እጅግ ስኬታማ ነበር ፣ብዙሐንን የያዘ ዓይወድቅምና። በተጨማሪም በዓመራሮቹ ለታዳሚው ስለድርጅቱ በቂ ማብራሪያ ከመሰጠታቸውም ሌላ የተለያዩ አዝናኝ የሆኑ ዝግጅቶች ቀርበዋል።በአጠቃላይ ኢትዩዽያውያን በኖርዌ እደግ ተመንደግ የሚያስብል ስራ ሲሰሩ ወያኔዎች ደግሞ እፍረት ሆኖባቸዋል።
   ኢትዮዽያ በክብር ለዘላለም ትኑር ሞት ለወያኔ።


                  
 




  

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes