Posts

Showing posts from June, 2022

Ethio 360 Zare Min Ale "ከብአዴን ብልጽግና የአማራ ሕዝብ ምን ይጠብቅ?" Tuesday June 28, ...

Image

Ethio 360 Zare Min Ale "ተጠናክሮ የቀጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞ" Saturday June 25, 2022

Image

Ethio 360 Zare Min Ale "ፓርላማውና የዐብይ አህመድ ስላቅ" Tuesday June 14, 2022

Image

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለለኝ ደብደባ ተፈፀመበት

Image
  ዛሬ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ፖሊስ በተለምዶ 3ተኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝቼ ነበር:: በዚህ እስር ቤት በታሳሪና በጠያቂ መካከል በሁለት ሾቦ የተጋረደ ከ10 ሜትር የሚበልጥ ርቀት አለ:: በታሳሪና በጣያቂ መካከል ባለው ርቀት የተነሳ፣ ንግግር ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው። አጠቃላይ ነገሩ መጯጯህ ነው:: ተመስገን ከዚህ በፊት በእስር ቤት እያለ ባጋጠመው በጆሮ ህምም ምክኒያት በዚህ ግር ግር ውስጥ ጆሮው ለመስማት ያዳግተዋል:: ይሄ በመሆኑ ተመስገን ለፖሊሶቹ "ትንሽ ቀረብ ብሎ ቢያወራኝ " ሲለው ፖሊሱ በእጁ የማመናጨቅ ምልክት አሳየው፣ ተመስገንም ድጋሜ ለማስረዳት ሲሞክር አንዱ ፖሊስ ከነበረበት ከጠያቂ ቦታ ሌላው ፓሊስ ከስረኛቹ መቆሚያ ደረጃ ላይ በመውረድ ለሁለት ተመስገንን አብረውት ከቆሙት እስረኞች መካከል ጎትተው በማውጣት በቦክስ፣ በጫማ ጥፊ ለሁለት ደብድበውታል። ይህ ሲሆን የሌሎች እስረኛ ጠያቂ ቤተሰቦችና እስረኞችም አይተዋል። ድብደባውን እየፈፀሙ ወደ እስራኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ ይዘውት ሄደዋል:: ከቆይታ በኃላ በቢሮ ውስጥ ተመስገንን ስናገኘው የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል:: አሁን ከእስር ቤቱ አስወጥተውኝ በሩ ላይ እገኛለሁ:: [የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሚዲያዎች ጉዳዮን እንድታውቁልን፣ ማጣራት አድርጋችሁ ለሕዝብና ለሚመለከተው አካል እንድታደርሱልን) ታሪኩ ደሳለኝ

111 ሚዲያዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ ፖሊስ ፍንጭ ሰጠ!!

Image
  የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ 111 የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን በሕገ ወጥነት ፈርጆ ለመዝጋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዛሬ ባወጣው ፍንጭ ሰጥቷል። ይህ ፍንጭ የተገኘው ፖሊስ ዛሬ ረቡዕ፤ ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም . ባወጣው መግለጫ ነው። መግለጫው መገናኛ ብዙሃኑን በስም ከመግለፅ የተቆጠበ ሲሆን፣ የመገናኛ ብዙሃን የስርጭት ፈቃድ ያልተሰጣቸው መሆኑን ጠቅሷል። እነኝህ መገናኛ ብዙሃን "ሕዝብን ከመንግሥት ለመነጠል ይሠራሉ" ሲልም እሮሮውን አሰምቷል። በዚሁ ምክንያት ፖሊስ 10 ጋዜጠኞችን አስሮ እያንገላታ መሆኑን አምኗል። በተግባር የታሰሩት ግን 19 ናቸው። በፕሬስ ነፃነት አዋጅ መሰረት ማንኛውም ጋዜጠኛ በሥራው ምክንያት ቢከሰስ እንኳን፤ ዶሴውን በውጭ ሆኖ መከታተልና መከራከር እንጂ በእስር ቤት እንዲቆይ አይገደድም። ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ / #ኢትዮጵያ

የአማራ ልዩ ኃይል አባላት፣ "ዘመነ እንዳይገኝ መረጃ እያወጣችሁ ነው" ተብለው እየተወነጀሉ ናቸው!!

Image
  መረጃ # የመንግስት ታጣቂዎች የሜጫን አካባቢ እያዋከቡ ነው ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ!! / የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) መሪ ዘመነ ካሴን ፍለጋ የገባው የመከላከያ ኃይል፣ ከአዴት ዴንሳ ባታ እስከ ብራቃት ያለውን መንገድ ወጥሮ ሕዝቡን እያዋከበ መሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። በጎጃም መራዊ አካባቢ የተሰማራው የመንግስት ታጣቂ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት ዘግቶ አርሶአደሩ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ ደንቃራ እስከመሆን ደርሷል። በዚህም ሳቢያ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እንደ ልብ ተንቀሳቅሶ የዕለት ከዕለት ስራውን ማከናወን አለመቻሉን ነው የአካባቢው ኗሪዎች የሚገልፁት። በህግ ማስከበር ሽፋን ሰላማዊ ህዝብን ማሸበር ባስቸኳይ ሊያቆም ይገባል ብለዋል። በሌላ በኩል፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት፣ "ዘመነን እንዳናገኝ መረጃ እያወጣችሁ ነው" ተብለው እየተወነጀሉ መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ናቸው። ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ / #ኢትዮጵያ

ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም እያሽከረከረ የነበረ ሹፌር ከእነ መኪናው በኦነግ/ ሸኔ ተቃጥሎ ተገደለ !!

Image
ፅንፈኞቹ የ12 ዓመት ህፃን አግተዋል!! / ትናንት ሰኞ ማታ፤ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ለዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 23 አጥቢያ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ጎጃም እያሽከረከረ የነበረ ሹፌር፣ ከእነ ኤፌ ኤስ አር መኪናው ጎሃ ፅዮን ከተማ ሊደርስ ጥቂት ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው በፅንፈኛው ኦነግ-ሸኔ ታቃጥሎ ተገድሏል። ረዳቱ በከፍተኛ ደረጃ ቆስሎ ታግቶ የቆየ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ወደ ህክምና መወሰዱንም የአካባቢው የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። ተሽከርካሪው "አማራ" የሚል ታርጋ እንደነበረውም ተረጋግጧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በዚያው በጎሃ ፅዮን ከተማ የኦሮሞ ፅንፈኛ አሸባሪዎቹ አንድ የ12 ዓመት አማራ ሕፃን ልጅን አግተው ወስደዋል። ሽብርተኞቹ በአካባቢው አንዳንዳንድ የአገዛዙ ባለሥልጣናት እንደሚደገፉም ምንጮች ጠቁመዋል። ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ / #ኢትዮጵያ

የባሕር ዳር ኗሪዎች ስንታየሁ ቸኮልን እንዳይጠይቁ ተከለከሉ !

Image
# # ከታገቱ 48 ሰዓት ቢያልፋቸውም ፍ/ቤት አልቀረቡም! / በባሕር ዳር ከተማ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ በአደራ እስረኝነት በግፍ ታግተው የሚኙት ስንታየሁ ቸኮል በወዳጅና ዘመዶቻቸው ብሎም በመላው የባሕር ዳር ኗሪዎች እንዳይጠየቁ ተከልክሏል። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊ የሆኑት አቶ ስንታየሁ፣ ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከታፈኑ ጀምሮ ዛሬ ከ48 ሰዓት በላይ የሆናቸው ሲሆን፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። ይባስ ብሎ የባሕር ዳር ከተማ ኗሪዎች በፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው እንዳይጠይቋቸው ተከልክሏል። በዚህም ምክንያት ምግብ እየገባላቸው አይደለም። ትዕዛዙ ከበላይ አካል መምጣቱም ተጠቁሟል። በተጨማሪም ጥቃት ሊያደርሱባቸው እንደሚችሉ የፖሊስ ሓላፊዎች እየዛቱባቸው መሆኑን የፖሊስ ጣቢያው የውስጥ ምንጮች አረጋግጠዋል። እስር ቤቱ ባሕር ዳር ውስጥ ካሉት ሁሉ በመጥፎነቱ የሚታወቅ ነው። / #ኢትዮጵያ