ከኢሳት ተገፍተው በወጡት ባለደረቦቻችን በሀብታሙ አያሌው፥ ብርታዊት ግርማዬ እና ኤርሚያስ ለገሰ ላይ እሮብ እለት ማለትም ግንቦት 28/2011 ዓም የተካሄደው ጥቃት በማን እንደተፈጸመ ፥ለምን ዓላማ እንደተፈጸመ እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም። ስለሆነም ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ ውጤቱን እስኪገልጽ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ እያሳሰብን ምርመራው ተጠናቆ ውጤቱ በፖሊስ ይፋ ሲደረግ ጉዳዩን ለሕዝብ የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን። በዚሁ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው እነዚሁ ባለደረቦቻችን በዋሽንግተን አድቬንቲስት ሆስፒታል ሕክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው የተመለሱ ሲሆን ከደረሰባቸው ቀላል የአካል ጉዳት በስተቀር ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ በዚሁ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes