![Image](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEgAYiQmCeD6lW4JkSv4-hUCj4_pj2G4htnQmMRBX6pcWwH-RGrxURLuF0k6OfLMAlH2YyPa0XdmDvB8YorcrCJsC6EDOGZFYzm-GtAriuiI_t0KvgrUiD_7K7XM_awMlC3cI9ZTG8AyHOw/s640/26112046_1751590534873021_7493403106177793939_n.jpg)
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 18/2010) በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ለማስታወስ በማህበራዊ ሚዲያዎች ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ታወቀ። በቲውተርና በፌስቡክ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ዘመቻ በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ሆነዋል። በየእስር ቤቱ በስቃይ ላይ የሚገኙትንና በግፍ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ፎቶግራፎች በመለጠፍና ስቃያቸውን በመዘርዘር ትኩረት እንዲያገኝ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። ዘመቻውን የሚያስተባብሩት በኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግለሰቦች እንደሆኑም ታውቋል። ዛሬ ፌስቡኩ በኢትዮጵያውያን አንድ ዘመቻ ተወሯል። መልዕክቱ ተመሳሳይ ሆኖ በዓለም ዙሪያ ባሉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲስተጋባም ውሏል። የዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የአቶ ኦኬሎ አኳይ፣ የወጣት ንግስት ይርጋ፣ የወጣት ሴና ሰለሞን፣ የአቶ በቀለ ገርባ፣ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የብ/ጄነራል ተፈራ ማሞና የሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች ፎቶግራፎች እየተለጠፉ በመታወስ ላይ ናቸው። ባለፉት 26 ዓመታት በህወሀት አገዛዝ በግፍ የተሰቃዩ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት የደረሰባቸው፣ ወደ እስር ቤት በህይወት ገብተው በሞት የወጡ አያሌ ኢትዮጵያውያን ዛሬ እየታወሱ የዋሉበት ቀን ነው ። የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ በኦነግ ስም የታሰሩ፣ በኦብነግ ተጠርጠረው የገቡ፣ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናችሁ ተብለው የሚሰቃዩና ሌሎችም በስም ተዘርዝረው የደረሰባቸው ስቃይና መከራ ተገልጾ እንዲታወሱ ተደርገዋል። በምርመራ ወቅት የእግርና የእጅ ጥፍሮቻቸው የተነቀሉባቸው፣ በብልታቸው ላይ የታሸገ ውሃ እንዲንጠለጠል የተደረገባቸ...