እኔ ማነኝ? ginbot7

Ginbot 7 Popular Force (GPF)

እኔ ማነኝ?

Home » Resource » እኔ ማነኝ?
Jul 19, 13 • by

እኔ ማነኝ?

ማሳሰቢያ

ይህን አነስተኛ ሰነድ የተወሰደው ከ220 ገጾች በላይ ርዝማኔ ካለው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የፖለቲካ ስልጠና ሰነድ ነው። ዋናው የስልጠናው ሰነድ እኔ፣ እኛና ህዝባዊ ሰራዊቱ፣ ሃገራችን ኢትዮጵያ፣ የፖለቲካና የፍልስፍና ጽንጸ ሃሳቦችና ንድፈ-ሃሳቦች በሚሉ 4 ምእራፎች የተከፋፈለ  ነው።  በዚህ ተቀንጭቦ በቀረበው ሰነድ ውስጥ የተነሱ ጉዳዮች አንዳቸውም ሳይቀሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ድርጅትና አባላት ብቻ ጉዳዮች ናቸው ብለን አናምን። የሁሉም የሃገራችን የፖለቲካ ድርጅቶችና አባሎቻቸው፣ እንዲሁም የአጠቃላይ የማህበረሰባችን ጉዳዮች ናቸው ብለን እናምናለን። በዚህ ሰነድ ውስጥ በተነሱ ጉዳዮች ላይ የግንቦት 7  ህዝባዊ ሃይል አባላት የሚያደርጉትን ሰፊና ጥልቅ ውይይት በትንሹም ቢሆን በማህበረሰባችን ውስጥ እንዲደረግ ካስቻልን ለሁላችንም ጠቀሜታ የሚኖረው መስሎናል። በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ የምንፈልገው በዚህ ሰነድ ውስጥ የተነሱ ችግሮች በመሰረቱ ሊቃለሉ የሚችሉት ተገቢ የሆኑ የስርአት ለውጦችና ተገቢው የሆኑ ተቋማት ሲመሰረቱ እንደሆነ እናውቃለን።  ቁልፍ  የሆኑት ከፖለቲካው ጋር የተያያዙ የስርአትና የተቋማት ለውጦች ናቸው። ከዚህ አንጻር ነገሮችን ካየናቸው ይህን አይነቱ ሰነድ ወይም ሌላ ምንም አይነት ሰበካ፣ ትንታኔ፣ ውይይት፣ የንባብና የምርምር ጥረት መሰረታዊ የሆነውን ለውጥ ለብቻቸው ያመጣሉ ብለን አናምንም። ችግሩ ያለው የምንመኛቸውን መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ስርአቶችና ተቋማት በሃገራችን የሉም። እነሱን ደግሞ  የምንፈጥራቸው እኛው የሃገሪቱ ዜጎች ነን። ይህ ሰነድ ሌላው ሁሉ ቢቀር በግለሰብ፣ በቡድንና በድርጅት ደረጃ ችግሮቻችን ምን ያህል ጥልቅና ውስብስብ እንደሆኑ መገንዘብ እንድንችል ያደርገናል የሚል እምነት አለን። ችግሮቹን ከተገነዘብን የመፍትሄዎቻቸውን ፍንጭ ለማየት አያዳግተንም። ስለሆነም ይህን ሰነድ ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ውጭ የሚገኙ ወገኖቻችን እንዲያነቡት በማሰብ በስፋት እንዲሰራጭ ወስነናል:: አንብባችሁ ሌሎች እንዲያነቡትና ውይይት እንዲያደርጉበት የተቻላችሁን ጥረት እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።

ሙሉ ጽሁፉን አንብበው ያስተላልፉት (Click Here: Ene Manegne-Who am I (pdf)

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes