ሰብአዊ መብት እና ፍትህ ለኢትዮጵያ ግብረ-ሐይል በአውሮፓ Task Force for Human Rights and Justice in Ethiopia – Europ


የሰብዓዊ መብት እና ፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረሐይል በሐገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኛው እና ፋሺስቱ ወያኔ በዜጎች ላይ የሚያደርሰውን መጠን የለሽ እስር፣ግድያ፣የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሐገር የማፍረስ ተልዕኮ በመቃወም ፍትሕ፣እኩልነት እና ነፃነት የሰፈነባትን የጋራ ሐገር ለመመስረት  በመላው የአውሮፓ ሐገሮች በተለያዬ መልክ  ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አክቲቪስቶች  የመሰረቱት ግብረ ሐይል ሲሆን ከተቁዋቁዋመበት ጊዜ አንስቶ በሐገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች በአምባ ገነኖች እና ዘረኞች 27 ዓመታት የጥፋት ሰይፍ ተስሎባቸው እና የመከራ ቀንበር ተጭኖባቸው የተለያየ የግፍ ፅዋ ሲጠጡ ፤ በየእስርቤቱ እየተወረወሩ በቃላት ተዘርዝረው የማያልቁ -ሰብአዊ የመብት ጥሰቶች እና መጠን የለሽ የዘር ፍጅቶች፣አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች ሲፈፀሙባቸው፣ከትውልድ ቀያቸው እየተፈናቀሉ ለስደት ሞት፣እንግልት እና ስቃይ ሲዳረጉ
ለሚያሰሙት የወገን ያለህ የድረሱልኝ  የሰቆቃ ጥሪ  ምላሽ በመስጠት ትላልቅ አውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፎችን በመጥራት ሕዝባዊ ውይይቶችን በማዘጋጀት እና የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በመስራት በሕዝብ ላይ ለሚደርሱ ሰቆቃዎች፣ ቁስሎች እና የድረሱልን ዋይታዎች የሕዝብ ድምፅ በመሆን ሐገርን ለማዳን በሚደረጉ ርብርቦች ሁሉ የበኩሉን ትልቅ አስተዋፅዖ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በተለይ ደግሞ ሕዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታበት የመጣዉን የመከራ ቀንበር መሸከም አቅቶት ከመሳሪያ አፈሙዝ ጋር ፊትለፊት እየተጋፈጠ ትግሉን አቀጣጥሎ የወያኔን ህልውና እያንኮታኮተ በመጣበት ወቅት ፋሺስቱ እና አምባገነኑ ስርዓት  የከፋፈለውን ሕዝብ የበለጠ በመከፋፈል እና የመጨረሻውን ኢትዮጵያን የማጥፋት ሕልሙን እውን የሚያደርግበትን የመጨረሻ ካርድ ስቦ ሐገራችን እልም ወዳለ የእርስ በርስ ግጭት እና ደም መፋሰስ ውስጥ በገባችበት ወቅት የችግሩን አሳሳቢነት ተረድቶ ምሁራኖች፣አክቲቪስቶች፣ታዋቂ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን፣የእምነት አባቶችን እና የአውሮፓ ፓርላማ ተወካይ የሆኑትን ሚስ አና ጎሜዝን ጋብዞ በመንትያ መንገድ ላይ ስለምትገኘው ኢትዮጵያ ሐገራችን ቀጣይ እጣፋንታ የተወያዩበትን ትልቅ መድረክ የአውሮፓ ማሕከላዊ ሐገር በሆነችው ጀርመን ፍራንክ ፈርት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ታህሳስ 9 እና 10/2017 የተካሄደውን የሁለት ቀን ጉባኤ አካሄዶ እንደነበር ሚታወቅ ሲሆን ይህንን የውይይት መድረኩን አስፍቶ የኢትዮጵያ እጣፈንታ ክፍል 2ን (ETHIOPIA FUTURE  PART 2) ሐገራችን አሁን በምትገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት ነገ ማለትም ጁላይ 3/2018 ከጠዋቱ 10:00 ጀምሮ ሊያካሂድ ዝግጅቱን አጠናቆ ታዳሚዎቹን በታላቅ ጉጉት እየጠበቀ መሆኑን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው።
 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት እና ፍትህ ግብረሐይል በአውሮፓ ይህንን የውይይት መድረክ ያዘጋጀው
ኢትዮጵያ ሐገራችን ከዚህ በፊት በእንጭጩ ተጨናግፈው የቀሩባትን የለውጥ ጭላንጭሎች በማስታወስ እና በማጥናት አንድ ሐገር ወደ ዲሞክራሲ የሚያመራ የለውጥ ጉዞ በሚጀምርበት ጊዜ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ተግዳሮቶች እና ስለመፍትሄዎቻቸው ምሁራኖች እና ሕዝብ ተሰብስቦ ሊወያይ እና ሊመክር የሚችልባቸው መድረኮች ሊፈጠሩ ባለመቻላቸው ነው በሚል እምነት ዛሬ ኢትዮጵያ የጀመረችው የለውጥ ጉዞ እና እያየች ያለችው ተስፋ ተጨናግፎ እንዳይቀር ምን መደረግ አልበት በሚለው እና በመሳሰሉት ላይ ማህበረሰባችን ከታዋቂ ምሁራን፣ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እና አክቲቪስቶች ጋር ይወያዩ እና ይመክሩበት ዘንድ መድረኩን አዘጋጅቱዋል።
እርሶም የወደፊትዋ ኢትዮጵያ ክፍል 2 (ETHIOPIA FUTURE  PART 2) ላይ በመገኘት የበኩሎን የዜግነት ግዴታዎትን ይወጡ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል
የሚቀርቡ ጥናታዊ ፅሁፎች:-
1. ለኢትዮጵያ ምን ዓይነት የፖለቲካ አስተዳደር ያዋጣታል (Option of political System for Future Ethiopia)
  አቅራቢ:-አቶ መሐመድ ሐሰን
2. የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት እና እንድምታውዎቹ(Ethio-Eretria Relations & Implications)
አቅራቢ:- የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ
3 የለውጥ ጉዞ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚና(Current Reform & Role of Opposition parties)
 አቅራቢ :-ዶክተር መራራ ጉዲና
4.ጭፍን አምባገነን መንግስት ሲለውጥ ያሉ ፈተናዎች፣እድሎችና የውደፊቱ አቅጣጫ(Transition from tyrannical government challenges opportunities & the way forward)
   አቅራቢ:- ዶክተር አሰፋ ነጋሽ
5. የኢኮኖሚ ነፃነት በኢትዮጵያ እና እድምታዎቹ(Economic Liberalization in Ethiopia & its Implication
   አቅራቢ:- ዶክተር ፈቃደ በቀለ
6. ወቅታዊ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎች(causes of Current Economic Crisis & way Forward)
አቅራቢ:- ዶክተር አክሎግ ቢራራ

ከዚህ ታላቅ የውይይት ዝግጅት በሁዋላ የኢትዮ ስቱት ጋርት ጀርመን ግብረሐይል ኦገስት ፫ እና ፬ምሽትን በዘመናዊ እና ባህላዊ ሙዚቃዎች ሲያዝናናዎት ሊያመሽ ልዮ የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ከብርቅየው ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሻምበል በላይነህ ጋር በጉጉት እየጠበቆት ነው።
ገቢው ለኢሳት
ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥር-00352691875832 እና በኢ.ሜል አድራሻችን ethiopiantaskforceeurope2016@gmail.comያገኙናል.
ነፃነት ፣ፍትሕ ፣እኩልነት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ሰብአዊ መብት እና ፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረ፡ኃይል በአውሮፓ ከጀርመን ስቱትጋርት ግብረ ኃይል ጋር በመተባበር

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes