ኢሳት መረጃ :-አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ፖሊሶች በስራ ሰዓት ሳይቀር በአደባባዩ እየተሰባሰቡ መረጃዎችን እየተለዋወጡ ነው። የደህንነት ሰራተኞችና የቀበሌ ሰራተኞች ስራ መስራት አቁመዋል። የቀበሌ ሰራተኞች በየመስሪያ ቤታቸው “ምን ይፈጠር ይሆን?” እያሉ በመነጋገር ጊዜያቸውን እያሳለፉ ነው።
በ አ/አ ዙርያ እስከ 20 ኪሎ ሜትር በሚደርስ እርቀት ላይ ባሉ ከተሞች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችና ከዚሁ አካባቢ ተነሰተው ወደ መሐል የሚመጡ ነጋዴዎች ወደ መሐል አዲስ አበባ መግባት አልቻሉም።
ጣፎ አካባቢ አሽከርካሬዎች ቤት ለቤት እየተፈለጉ ስራ እንዲጀምሩ ቢጠየቁም አሻፈረን ብለዋል። የኦሮምያ ክልል ሰርቪስ መኪናም አገልግሎት አቁሟል።
መረጃ ደቡብ
በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ተፈጥሯል። የምግብ ሸቀጦች ዋጋና የቤት ኪራይ ጨምሯል። የቡና እና የጫት ንግዱ ተቋርጧል።


Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes