ለትግሉ:- አስተዋፅዖ የምናደርግባቸው መንገዶች የተለያዮ ሊሆኑ ይችላሉ

   

ለትግሉ:- አስተዋፅዖ የምናደርግባቸው መንገዶች የተለያዮ ሊሆኑ ይችላሉ።
ለምሳሌ;- ከፊሉ በገንዘብ የማይተመን ህይወቱን ሲሰጥ ከፊሉ ደግሞ በሙያው እና በእውቀቱ አስተዋፅ  ያደርጋል፣ ሌላው ደግሞ  የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ  ለትግሉ ያለውን አጋርነት ያሳያል።
ለትግሉ አስተዋፅዖ የምናደርግባቸው መንገዶች የተለያዩ ይሁኑ እንጅ ግባችን ግን አንድ ነው!
      ነፃነት
እንግዲህ ለዚህ ለነፃነት ለሚደረግ የትግል ጉዞ ደግሞ ሚዲያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
የናዚ ወያኔም ሰው በላ ሥርዓት የሚዲያን ወሳኝነት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው ሚዲያዉን ተቆጣጥሮ የፈለገውን እና የሚመቸውን ፕሮፓጋንዳ እየነዛ በሕዝብ እና በሐገር ላይ ከፍተኛ ሸፍጥ እየፈፀመ የሚገኘው።
ይህ ፋሺስት ስርዓት ሐገር ሸጥዋል፣ትውልድ እንደቅጠል አርግፉዋል ፣በሺዎች የሚቆጠሩ ወግኖቻችን  በየእስር ቤቱ ይህ ነው የማይባል እና በቃላት ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል እየተፈፀመባቸው የወገን ያለህ እያሉ ነው፣የመኖር ህልውናችንን አሳጥቶ በስደት በየበረሀው እንድንታረድ አድርጎናል*፤ለዚህ ብሄራዊ ውርደታችንም አታልቅሱ፣አታውግዙ ተብለን በአደባባይ ተደብድበናል ፣የሐገራችንን አንጡራ ሐብት መዝብሩዋል፣ታሪካችንን አውድሙዋል፣ብሄራዊ ማንነታችንን አሳልፎ ሰጥቱዋል፤የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ተፈፅመዋል፤የበደኖው፣የጋምቤላው ሰቆቃ ፣የኦሮሞ እና የሶማሌ ወገኖቻችን እልቂት የሚረሳ አይደለም።
እንግዲህ ይህ የወገን ሰቆቃ እና መከራ እንቅልፍ የነሳቸው ወገኖቻችን ናቸው ለታፈነው ሕዝባችን አይን እና ሆኖ የሚያገለግለውን ኢሳትን ያቁዋቁዋሙልን።
ኢሳትም  እውነቱን እየጎለጎለ የወያኔን ሸፍጥ እና ሴራ ለሕዝብ ግልጥልጥ አድርጎ የሚያሳይ ፤ለመላው ኢትዮጵያዊ ልሳን የሆነ ተፅእኖ ፈጣሪ ሚዲያ ሆኖ መገኘቱ መላው ወያኔን እና ቡቹሎቹን ምጥ ውስጥ ከቱዋቸው ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ መድበው ህልውናውን እየተፈታተኑት ይገኛሉ ነገር ግን ኢሳት የሕዝብ ነውና በሕዝብ ድጋፍ ፈተናዎቹን ተቁዋቁሞ 7 ዓመቱን በመላው አለም እያከበረ ነው።
 እነሆ ኖርዌም እድሉ ደርሱዋት Otober14/2017 የኢሳትን ሰባተኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እያለች ነው።
 ስለዚህ ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው የልጆቻቸውን ሕይወት ለማቆየት የደረቀ ጡታቸውን እያጠቡ አስፋልት ዳር የተኙትን እናቶች ፣ድምፅ አልባ የሆነውን፣ሳይማር ያስተማረንን፣እና ወያኔ እየፈፀመብን ያለውን በቃላት ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል እያሰብን ለታፈነው ሕዝባችን ልሳን ሆኖ እያገለገለ ያለውን  ኢሳትን ለመደገፍ  October 14/2017 ኦስሎ ኖርዌይ እንገናኝ።
የኢሳት ኢዲቶሪያል ሐላፊ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔ ያለም በመሀከላችን ተገኝቶ የኢሳትን 7ዓመት ጉዞ የሚያስዳስሰን ሲሆን ተወዳጅዋ ድምፃዊት ሐኒሻ ሰለሞን ከኦርጋኒስት መርሶ ወንድማገኝ ጋር በመሆን በዓሉን በጣመ ዜማ እስከ እኩለ ሌሊት ታደምቀዋለች።
ይምጡ እየተዝናኑ የኢትዮጵያውያን አይን እና ጆሮ የሆነውን ኢሳትን ይደግፉ!!!
 

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes