ኩባውያን ለኢትዮጵያ 

ይህ የምትመለከቱት ቪዲዮ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1969 እስከ 1970ዓ.ም የሶማሊያው መሪ ሜጀር ጄኔራል ሞሃመድ ዚያድ ባሬ ሰራዊቱን አሠማርቶ ታላቂቱን ሶማሊያ ለመመስረት በሚል የቀን ቅዘት ኢትዮጵያን ወሮ በነበረበት ወቅት የደረሱልን በፕሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ የሚመሩት የኩባ የጦር ኃይላት ከሰራዊታችን ጎን በመሆን የሁለቱም ሐገራት ሕዝብ መዝሙር ከተዘመረ በሁዋላ ከሶማሌው ወራሪ ሐይል ጋር ሲዋደቁ የሚያሳይ ነው።
                           ( በውቅቱ በጦርነቱ ላይ ተገኝቶ የኩባ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ የቀረጸው ቪዲዮ)
ስለ ኢትዮጵያ ነፃነት ሲሉ የሶማሌን ወራሪ ኃይል ድባቅ ለመምታት ሐገራትን አቁዋርጠው ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን በመቆም ሲዋደቁ የነበሩትን እነዚህን ኩባውያን እዚህ ቪዲዮ ላይ ስመለከትም ሆነ ኩባ ለኢትዮጵያ የዋለችውን ውለታ ሳስብ የሚሰማኝ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ሲሆን:-
ይሄውም:-1ኛው በቃላት ተገልፆ የማያልቅ ለኩባውያን ያለኝ ታላቅ አክብሮት ሲሆን:-
            2ኛው ስለኛ ዳር ድንበር ሲሉ ኩባውያን ሕይወታቸውን የገበሩላት የዛሬዋ ኢትዮጵያ ወጣቶች ወያኔ የተባለ ፤ባንዳ የባንዳ ዘር ፤አያት ቅድማያቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው ዳርድንበሩዋን ጠብቀው ያቆዩልንን ኢትዮጵያ መሬትዋን እየቆረሰ ለባእዳን በመሸጥ ላይ ያለ እና በሕዝባችን ላይ የባርነት ቀንበር ጭኖ ሐገር በመመዝበር ላይ ያለን ፋሺስት ወያኔን የመሰለ ጠላት ቁጭ አድርጎ አርሴናል ገለመኔ እያለ የሚያወራውን እና ባህል እና ስርዓቱን ትቶ በተለያዩ ሱሶች የተጠመደውን ወጣት ሳስብና ሳይ አይ!!! ኢትዮጵያ እያልኩ ልቤ በሐዘን ይደማል፤ መተንፈሻ ትናጋውን ለታነቀ ሕዝብስ ስለ አርሴናል ገለመኔ ማውራት ምን ይፈይድለታል?የሚልም ጥያቄ ሁል ጊዜ በውስጤ ይመላለሳል።
 

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes