በኬንያ ስደተኞችን ይሰልሉ ነበር የተባሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ


ባሳለፍነው እሁድ ናይሮቢ ኢስሊ የተበለ ቦታ የከተሙ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰማራቸው ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል፡፡
በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ግለሰቦቹን በተመለከተ ሲያቀርቡት የነበረው ጥቆማ በመጨረሻ ሰሚ ጆሮ በማግኘቱ የኬንያ የጸረ ሽብር ግበረ ሀይል ግለሰቦቹን ከያሉበት ለቃቅሞ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ስደተኞቹን አስደስቷል፡፡ታሳሪዎቹ በቀጣዩቹ ቀናቶች ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የሚጠበቅ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት በኢምባሲው አማካኝነት ከፖሊስ ሐላፊዎች ጋር ግኑኝነት መጀመሩ የፍርድ ሂደቱን እንዳያስተጓጉለው ብዙዎች ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት ከኬንያ ተጠርንፈው ወደ አገር ቤት የተወሰዱ ሰዎችን የተመለከተ ሪፖርት ለመንግስት ያቀርቡ እንደነበርም ለመረጃው ቅርበት ያለቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡
በመጪዎቹ ቀናቶችም ጉዳዩን የተመለከተ ዘርዘር ያለ መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡

https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2015/06/17/xcz/ 

 

Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes