የትግሬ እና የኦሮሞ ልሂቃን፣ ዐማራን በጅምላ ለመፍጀት የቀየሱት የተጠቂነት ፖለቲካ ሥልት
ለመሆኑ የተጠቂነት ፖለቲካ ሥልት ምን ማለት ነው? የተጠቂነት ፖለቲካ ሥልት፣ የአንድ ማኅበረሰብ ልሂቃን፣ ባልነበሩበት እና ባልኖሩበት የታሪክ ዘመን፣ በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ጉዳዮች አስገዳጅነት የተፈጠሩ ግጭቶችን እና የተከሰቱ ክስተቶችን ለማብራራት የተጣመመ ትንታኔ በማቅረብ፣ ለራሣቸው የፖለቲካ ዓላማ ማሣኪያ አድርገው የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። እኒህ ልሂቃን በግጭቶቹ ወቅት ራሱም ጉዳት ደርሶበት፣ ነገር ግን የድል ባለቤት የሆነው አካል የወሰዳቸውን ዕርምጃዎች፣ ትክክለኞቹን ከሐሰት ፈጠራዎች ሣይለዩ፣ እንዲያውም ልብ ወለድ ድርሣኖችን በመጨማመር፣ «ይህ ተፈጸመብን፣ እንዲህ ተደረግን፣ ይህን ተቀማን፣ ይህ በደል ደረሰብን፣ እንዲህ ይሉናል፣ ወዘተርፈ» እያሉ ያልተባሉትን እንደተባለ በማራገብ፣ ያልተደረገውን እንደተደረገ በማቅረብ፣ «ተምኔታዊ ተጠቂነትን» እንደ ኃይል ማሰባሰቢያ ሥልት ይጠቀሙበታል። ይህ ዓይነቱ ዘዴ ለነገዳቸው አባሎች የሥነልቦና የበታችነትን፣ ተዋራጅነትን እና ተሸናፊነትን የሚያሸጋግር ከመሆኑም በላይ፣ ትውልዱ ትናንትን እንጂ ነገን እንዳያይ በመሸበብ፣ ለ«ተበደልኩ» ባዩም ሆነ «በዳይ» ለተባለው ወገን የወል መጠፋፊያ የሚሆን የበቀል ጎዳናን ይጠርጋል። የዐማራው ነገድ በየዘመኑ በተለያዩ የውጪም ሆነ የአገር ውስጥ ኃይሎች ከፍተኛ የሆነ ግፍ እና በደል የተፈጸመበት መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። የዐማራው አባቶች ግን ምንጊዜም ቢሆን ለልጆቻቸው «የእነ እገሌ ነገድ/ጎሣ እንዲህ አደረጉን»፣ ወይም «እንዲህ ይሉናል» የሚል የሥነልቦና እና የሥነምግባር ስብራትን የሚፈጥሩ ትውፊቶችን ለልጆቻቸው አያስተላልፉም። በመሆኑም በተጠቃም ጊዜ ቢሆን ዐማራው በሥነልቦና እና ሥነምግባር ደረጃ በአጥቂዎቹ ላይ የበላይነቱን እንደያዘ እንዲቀጥል አድርጎ...