#Ethiopa_AddisAbaba ቀናት ካስቆጠረው የእናቷ አስከሬን ጎን ተቀምጣ!

 ♦️እንግዲህ ከእኒህ ዓይነቶቹ ጋር ነው ጥምረት ቅብርጥስዮ የምትለን እስከዛሬ ደብዛቸው የጠፋው የደንቢ ዶሎ እህቶቻችን እና በአራጆችዋ ፊት ቆማ ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም እያለች እየማለች እና እየተገዘተች የታረደችው ህፃንዋ አይሻ እና መሰሎችዋስ አይፋረዱህም???


         ☆☆☆☆☆


♦️በሚኮላተፍ የህፃን አንደበቷ "እራበኝ፣ እራበኝ" እያለች የሲቃ ድምፅ ታሰማለች፣ ቀናት ካስቆጠረው የእናቷ አስከሬን ጎን ተቀምጣ!


እናቷ የተገደለችው እለተ አርብ ነሀሴ 15/2018 ዓ/ም ነው። ህፃኗ ልጅ ከእናቷ አስከሬን ጎን ተቀምጣ የተገኘችው ሰኞ ነሀሴ 18/2018 ዓ/ም አመሻሹን ነው። ወልጅ እናቷን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ገዝግዘው የገደሏት እነዛ ጨካኞች ህፃኗን ልጅም ታፋዋ ላይ ክፉኛ አቁስለዋታል።


ከጥቃቱ በኋላ በሕይወት የተረፈ ሰው ካለ ለማገኘት አከባቢውን ሲያስሱ የነበሩ ሌሎች የአማራ ተወላጆች ወደ ልጂቱ ሲቀርቡ ...እነዛ እናቷን ያለርህራሔ የገደሉባትና እሷንም ጭኗ ላይ ያቆሰሏት አውሬያዊ ባህሪ ያላቸው ጨካኞች መስለዋት ...በፍርሀት ትንቀጠቀጥ ነበር ልጂቱ።


ከእናቷ አስከሬን ጎን እንደተቀመጠች በሚኮላተፍ የህፃን አንደበቷ "እራበኝ፣ እራበኝ" እያለች በተደጋጋሚ የሲቃ ድምፅ ታሰማለች።


የግፍ ፅዋው ሞልቶ የፈሰሰበት ምድር፣ የፍትሕና የእዝነት ሚዛን ተዛብቶ የሰው ልጅ የጭካኔ ጥግ እስከምን ድረስ እንደሆነ የታየበት ወለጋ!




Comments

Popular posts from this blog

Black Grazziani Abiy Ahmed Defeated Unarmed Ethiopians At The Battle Of MENELIK Square On Adwa Victory Day !

Ethiopia: Crushing Freedom Creating Fear BY GRAHAM PEEBLES

የአቶ ስብሐት ነጋ እብደት ምነው ሕክምና ተነፈገው?