♦️አንድ ጥያቄ := መመለስ ከቻላችሁ መልሱ!
♦️ማለቴ መልሳችሁ ዝምታ ከሆነ ግን ልክ እንደኔ እራሳችሁ ለራሳችሁ በውስጣችሁ ያለው መልስ:=
♦️ ይህን ጥያቄ እንኳን እኛ በአማራ ሕዝብ ደም እና አፅመ ርስት ላይ እየተሳለቀ ያለው እና የህልውና ትግሉን አሳልፎ ሽጦ ከአራጆቻችን ጉያ የተወሸቀው ዘመነ እና ግብረ አበሮቹም በትክክል አይመልሱትም የሚል ነው ማለት ነው።
♦️ጥያቄው ምን መሰላችሁ:=
♦️ ትላንት አንድ ስልክ ተደውሎልኝ ነበር ፤ በአሁኑ ሰአት ጡረታ የወጣ ጋዜጠኛ ቢሆንም አሁንም በሚፅፋቸው ፅሁፎች ጭምር በጣም ተፅኖ ፈጣሪ ነው ።
♦️እና ይሄውላችሁ ሰላምታ ከተለዋወጥን በሁዋላ የሺሐረግ አሁን የደወልኩልሽ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ነው አለኝ!
♦️ ስለምን ብየ ጥያቄውን በጥያቀ መለስኩ!
♦️እንዲህ ሲል ጠየቀኝ በዜና ላይ ሌሎች ኃይሎችን ጨምሮ ፋኖ ከTPLF እና ከ OLF ጋር ስምምነት አድርጎ በጋራ የአብይ አህመድን አገዛዝ ለመጣል ትግል እያደረጉ ነው የሚል ሲሆን:=
♦️♦️እስክንድር ግን ይህንን አልተቀበለውም ይላል ስለዚህ አሁን የምጠይቅሽ:=
♦️ የዘር ጭፍጨፋ አደረጉብን ከምትሉዋቸው ኃይሎች ጋር ፋኖ ያደረገው ስምምነት በምን ላይ ነው? የሚል ነበር።
☆☆☆☆☆
♦️የኔ መልስ ይሄውልህ:= በመጀመሪያ ደረጃ የኔን አቋም ልንገርህ እነ CNN BBC እና ሌሎች ትልልቅ ሚዲያዎችን ጨምሮ ማንም ዘገበውም አልዘገበውም አሰቃቂ እና ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋዎች ተካሂደውብናልም እየተካሄዱብንም ነው ፤ ከነዚህ ኃይሎች ጋር ምንም የአይዶሎጂ ልዩነት በሌለው ስልጣን ላይ ባለው የአብይ አህመድ አገዛዝ ጭምር እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ በአማራ ሕዝብ ላይ እጅግ አሰቃቂ የሆነ ከፍተኛ የዘር ፍጅት ወንጀሎች እየተፈፀሙ ነው!!!
♦️ እነዚህ ኃይሎችም ወያኔTPLF የትግራይ ነፃ አውጭ ነኝ ብሎ መጥቶ የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ሲቆጣጠር ኢትዮጵያ ሐገራችንን የሚበትን ፤ለእነሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም እስከ መገንጠል መብት የሚሰጥ እና ኢትዮጵያን ብትንትኗን የሚያወጣ አንቀጽ 39 የሚሉትን አንቀጽ አስቀምጠዋል ፤ እነዚህ ኃይሎች አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው፤ ለአማራውም ፤ ለለጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ለአዲስ አበቤውም አደጋ የሆኑ የሽብር ቡድኖች ናቸው!!!
♦️ስለዚህ ይህን ጥያቄ ስትጠይቀኝ በአራጆችዋ ፊት ቆማ ላለመሞት ስትል ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም እያለች የታረደችውን ህፃን አይሻን ፤ የአማራ እና የክርስቲያን ልጅ አይወለድም እየተባለ ሆድዋን ተቀዳ ፅንስዋን ያወጡባትን አማራ ሴት እና ከዚህ በፊት በፎቶ እና በቪዲዮ ጭምር ያሳየሁህን የጅምላ ጭፍጨፋዎችን ፤ እንደከብት በሰይፍ እየታረዱ ስጋቸው እየተቆራረጠ ላውሬ የሚጣሉትን፤ አሰቃቂ ፆታዊ ጥቃቶች የሚፈፀምባቸውን እና እራሳቸውን እየተጨፈለቁ በአሰቃቂ ሁኔታ የፈጁዋቸውን የአማራ ህፃናት እና ሐገርሽህን ብትንትኗን ልናወጣ ነው የመጣነው የሚሉኝን እነዚህን አፍራሽ ኃይሎች እያሰብክ ጠይቀኝ !
♦️♦️ ስለዚህ መልሴ ሊሆን የሚችለው የአማራ ኮዝ እና የነዚህ ተጣመሩ ምናምን የሚባሉት ኃይሎች ጥያቄ አንድ ዓይነት ስላልሆነ አልቀበለውም!!! ♦️የሚል ሲሆን አሁን ተፈጠረ የሚባለው ጥምረትም ይበሉት ትብብር በሁለት ጎራ ከፍሎ እያጨቃጨቀን ነው !!!
♦️በተረፈ ከነዚህ ኃይሎች ጋር በምን እና እንዴት ተስማማ የሚለውን እራሱን ዘመነን ብትጠይቀው አልኩት!!! ።
♦️አቦ ይመቸን! ጭዌዋ እዚህ ጋ ነው ያለችው := "እስክንድር ግን እንዳልተቀበለው እና እንደሌለበት በዜና ሰማሁ ያለኝ" ይህ ጋዜጠኛ "ማነው ዘመነ"?
አይለኝ መሰላችሁ።
አይ ዘመነ እውቅና በዓላማ ፅናት፤ ሆኖ በመገኘት እና በስራ እንጅ መች እስክንድርን በማሳደድ ፤ በእስክንድር ላይ ዘመቻ በማስከፈት ፤ የራስ የትግል ጏዶችን በመግደል ፣በማፈን ፣የቁም እስረኛ አድርጎ በማሰቃየት እና የሕዝብን የህልውና ትግል ሽጦ ከጠላት ጉያ በመወሽቅ ሆነና!!!
♦️♦️ለማንኛውም ልላችሁ የፈለኩት እናንተ ብትሆኑ ስምምነቱ በምን ላይ ነው?? የሚል ጥያቄ የተጠየቃችሁት መልሳችሁ በትክ ክል ምንድነው??
☆☆☆☆☆
♦️በዚህ አጋጣሚ እስክንድርን እያሳደዳችሁ #ከኦነግ(OLF) እና #ከወያኔ(TPLF) ጉያ ለተወሸቃችሁት ለነዘመነ እና ለግብረ አበሮቹ እዩ ከናንተ ይልቅ በዓላማ ፅናቱ፤በከፈለው ትልቅ የነፃነት የትግል ዋጋ ፤በዓለም አቀፍ ደረጃ ሽልማቶችን እስከማሸለም ያደረሰው የጋዜጠኝነት ሙያው እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪነቱ ብቻውን እንደ ተቋም ያገዘፈውን እስክንድርን ጫፉን ብትነኩት ወይም ብታስነኩት ማንነታችሁን ፍንትው አርጎ ስለሚያሳይ:= ፀባችሁ ከኛ ጋር ብቻcስለማይሆን ተጠንቀቁ እንላለን።
ለማንኛውም ወገን ከላይ የተጠየኳትን ጥያቄ ማለቴ በምን ተስማሙ የምትለዋን እናንተ ብትጠየቁ መልሳችሁ በትክክል ምንድን ነው???
♦️ ይህን ጥያቄ ዘመነ እራሱ ቢጠየቅ በትክክል አያውቀውም ነው? ወይስ በመርህ አልባ ጋብቻቸው ውስጥ ያለውን የነዘመነን ስምምነት በትክክል እናውቀዋለን ብላችሁ መመለስ ትችላላችሁ???
💚💛❤️
#viralreelschallenge #viralpost #Ethiopa #AddisAbaba #Fano

Comments
Post a Comment