Ethiopia_Amhara መቆሚያ ያጣው የደም በልፃጊው የኦነጉ የዐብይ አህመድ አፈና

 #ዜና

# ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ታሰረች!! # ስንታየሁ ቸኮል በኦሮምኛ ተናጋሪ ሰላዮች መታፈኑ ተረጋገጠ !! / ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ዛሬ ቅዳሜ ጧት፤ ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገዛዙ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ውላለች። መዓዛ አዲስ አበባ፤ ሰሚት ከሚገኘው የጓደኛዋ ቤት ውስጥ የፌዴራል ፖሊስን ልብስ በለበሱ እና ሲቪል በለበሱ ፖሊሶች ነው የተወሰደችው። በተያያዘ ዜና፣ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከአዲስ አበባ ለዚሁ ተግባር ከቤተ መንግሥት ስምሪት ተቀብለው በመጡ ኦሮምኛ ተናጋሪ የመንግሥት የስለላ ሠራተኞች ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ መታፈኑ ተረጋግጧል። አቶ ስንታየሁ በአሁኑ ጊዜ በባሕር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፤ አቢሲንያ ባንክ አጠገብ በሚገኘው 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ ይገኛል። በዚህ የታሰረው በአደራ እንደሆነ እና ወደ አዲስ አበባ እንደሚወስዲት አፋኞቹ የነገሩት መሆኑንም ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በእስር ቤቱ ተገኝተው ለጠየቁት ተናግሯል። እስር ቤቱ አስቀድሞ አክቲቪስት ቲና በላይ የታሰረችበት ሲሆን፣ ከስንታየሁ ቸኮል ጋርም በርቀት ተገናኝተዋል። ስንታየሁ ባልደራስ ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት በሚያደርገው ጉዞ የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ንቅናቄውን ለመስተባበር አስቀድሞ ባሕር ዳር መግባቱ ይታወቃል። / #ኢትዮጵያ


Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes