ጥግ የደረሰው የኦሮሞ ፅንፈኞች የተረኝነት ስሜት

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለሀምሌ 11 ተቀጠሩ- ምግብ እና ልብስ እንዳይገባላቸው መከልከላቸውን ጠበቃቸው አቶ አዲሱ ጌታነህ ገለጹ።
ዛሬ ሀምሌ 1 ቀን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኢ/ር ይልቃልን ሂደው እንደጎበኟቸው አቶ አዲሱ ለአማራ ሚዲያ ማእከል ገለጹ።3ኛ ፖሊስ ጣቢያ (አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን) የታሰሩት ኢ/ር ይልቃል ፍርድ ቤት ቀርበው "በአዲስ አበባ ለተነሳው ሁከት እና ግርግር ለሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም ምክንያት ሁነሀል " በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው ለሀምሌ 11 ቀን እንደተቀጠሩ ጠበቃቸው አቶ አዲሱ ከዶ/ር ዳንኤል በቀለ መስማታቸውን ገልጸዋል። ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው መከልከላቸውን እና ምግብም ሆነ ቅያሪ ልብስ ስላልገባላቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ሊጠይቋቸው ሲሄዱ አይቻልም እንደሚሏቸው እና አንዳንዴ ደግሞ እዚህ የለም እንደሚሏቸው የገለጹት ጠበቃ አዲሱ በደንበኛቸው የተፈጸመው የመብት ጥሰት አሳሳቢ ነው ብለዋል።
የኦፌኮ አመራሮችን ሰው እንደሚጠይቃቸው እና ገደብ እንደሌለባቸው የሚታወቅ ሲሆን በአንጻሩ የኢሀን ሊቀመንበር በሆኑት በኢ/ር ይልቃል ጌትነት ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ተደርገዋል።



Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes