ሰብአዊ መብት እና ፍትህ ለኢትዮጵያ ግብረ-ሐይል በአውሮፓ Task Force for Human Rights and Justice in Ethiopia – Europ
![Image](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEhjcxSCJmPAH4yBJsqgrUcnOft9VuX_ejRUUlXgwrC1Y_fJyKCKAEc_uwFsHJppWYZiz-tQdklVtr1YgnnhdEt6asj33X9r0J3NwbhomE-MumJyZGy4xnOhdiRE0O4XPwse5Yl1ABLDC6U/s200/37867887_881554335361633_3561590175530221568_n.jpg)
የወደፊትዋ ኢትዮጵያ ጉባኤ አዘጋጅ ግብረ ኃይል መግለጫ -2018 ስቱትጋርት - ጀርመን ETHIOPIA FUTURE CONFERENC PRESS RELEASE -2018 Stuttgart-Germany የሰብዓዊ መብት እና ፍትሕ ለኢትዮጵያ ግብረሐይል በሐገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኛው እና ፋሺስቱ ወያኔ በዜጎች ላይ የሚያደርሰውን መጠን የለሽ እስር፣ግድያ፣የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሐገር የማፍረስ ተልዕኮ በመቃወም ፍትሕ፣እኩልነት እና ነፃነት የሰፈነባትን የጋራ ሐገር ለመመስረት በመላው የአውሮፓ ሐገሮች በተለያዬ መልክ ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አክቲቪስቶች የመሰረቱት ግብረ ሐይል ሲሆን ከተቁዋቁዋመበት ጊዜ አንስቶ በሐገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች በአምባ ገነኖች እና ዘረኞች ለ 27 ዓመታት የጥፋት ሰይፍ ተስሎባቸው እና የመከራ ቀንበር ተጭኖባቸው የተለያየ የግፍ ፅዋ ሲጠጡ ፤ በየእስርቤቱ እየተወረወሩ በቃላት ተዘርዝረው የማያልቁ ኢ - ሰብአዊ የመብት ጥሰቶች እና መጠን የለሽ የዘር ፍጅቶች፣አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች ሲፈፀሙባቸው፣ከትውልድ ቀያቸው እየተፈናቀሉ ለስደት ፣ ሞት፣እንግልት እና ስቃይ ሲዳረጉ ለሚያሰሙት የወገን ያለህ የድረሱልኝ የሰቆቃ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ትላልቅ አውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፎችን በመጥራት ፣ ሕዝባዊ ውይይቶችን በማዘጋጀት እና የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በመስራት በሕዝብ ላይ ለሚደርሱ ሰቆቃዎች፣ ቁስሎች እና የድረሱልን ዋይታዎች የሕዝብ ድምፅ በመሆን ሐገር...