በሶስተኛው ይሁዳ ጣላችሁ ክቡራት እና ክቡራን የዚህ ፅሁፍ ተከታታዮቼ በያላችሁበት ሰላምታዬ ይድረሳችሁ እያልኩ መቼም የሐገር ነገር ሆድ ይፍጀው ተብሎ ዝም የሚባል ባለመሆኑ እየሆነ ስላለው እና ስለተሰማኝ ስሜት ትንሽ ልል ወደድኩ ሐገር ማለት እናት ናት !!! ሐገር ማለት ሁሉሉ ሉ …. ነገር ናት ! የሐገርን ሉአላዊነት ማስከበር ደግሞ ከሰንደቅ ዓላማዋ ይጀምራል፤ ለዚያም ነው ጣልያኖች በ 1928 መላው ኢትዮጵያን ወረው ከአስመራ ለትርጉም ወሰደውት የነበረው ጀግናው ዘርዓይ ደረስ ከእለታት ባንዱ ዓመታዊ በአላቸው ላይ የሃገሩን የአርበኝነት ዩኒፎርም እስከነ ሙሉ ትጥቁ ጎራዴውን ጨምሮ ለብሶ በዓሉ ቦታ እንዲገኝ ካረጉት በሁዋላ የእምዬ ኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መሬት ላይ አንጥፈው እየተፉ ሲያልፉ ጎራዴውን መዞ አጠገቡ ካሉት ወታደሮች በመጀመር የጣልያን ሹማምንቶችን አንገት እየቀነጠሰ በመጣል ታላቅ ገድል የሰራው . አዎ !!! በከፍተኛ የሐገር ፍቅር ስሜት እንደነበልባል እሳት ውስጡ እየተንቀለቀለ በታላቅ ቁጣና እልክ የመዘዘውን ጎራዴ ከሀፎቱ ማስመለስ የሚችል አንዳችም የሰው ሀይል እንደሌለ የተረዱት ጣልያኖች በጥይት እግሩን መተው እስኪጥሉት ድረስ አርበኛችን ዘርአይ ደረስ ብቻውን ይህንን ገድል ፈፅሙዋል !!! ታዲያ ምነው እናንተ ? ለዛሬው ፅሁፌ እና ለዚህ ጥያቄዬ መነሻ የሆነችኝ ከወደ ጀርመን አካባቢ ስትንከባለል ያየሁዋት ፅሁፍ ስትሆን እንዲህ በማለት ትጀምራለች :- “ ውድ የመማክርት ጉባኤ አባላ...