Posts

Showing posts from August, 2017
Image
የወገኖቻችን ቁስል የሚሰማው ለእኛ እንጅ ለናዚዎች አይደለም!!!        THEY ARE THE REASON! ነሀሴ 4 ቀን 2009 ዓ . ም በአሳዛኝ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ወደ የመን ሊሻገሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ሆን ተብሎ በታጣቂዎች እባህር መወርወራቸውን ESAT እና "VOA" ዘግበዋል፥ ጄኔቫ የሚገኙትን የ IOM ቢሮ ቃል አቀባይንም አነጋግረዉ ወደ ስፍራው የሚሄድ ልኡካን ቡድን ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል። ይህ ዓይነቱ ክስተት የመላ ኢትዮጵያዊን ቅስም የሚሰብር እና አንገት የሚያስደፋ ከሀዘንም በላይ ሀዘን ቢሆንም በተለይ በቅርብ ሆነው ባህር የሚተፋውን የወገኖቻቸውን እሬሳ እየጠበቁ በመቅበር ላይ ላሉት ወገኖቻችን ይከብዳል። ከ180-160 በሚደርሱ ኢትዮጵያውያኖች ላይ የተከሰተ ይህ አደጋ ለናዚዉ ወያኔ ስርዓት   ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ግን ለዜና እንኩዋን ብቁ ሆኖ ባለመገኘቱ በግብፅ በባቡር አደጋ ስለሞቱት 41 ሰዎች ነው እያወራ ያለው። *መንግስት በሌለበት ሐገር ሕዝብ መንግስት ሆኖ መነሳት አለበት!!! የወገኖቻችን ጥቃት ጥቃታችን ፣ቁስላቸው ቁስላችን ነው፤ሁላችንም የችግሩ ተጠቂዎች ነን ። በናዚው ወያኔ ሐገር መነጠቃችን ያመጣብን ጣጣ በየደረስንበት ሞት፣ስቃይ፣ ጉስቁልና ፣ ውርደት ብቻ ሆኑዋል። አንዳንድ የዓለም ሐገራትም ከወያኔ ጋር ባላቸው የጥቅም ትሥሥር ምክንያት በሐገራችን ያለውን የወያኔ አፓርታይድ አገዛዝ ሀጢያትን እየሸፈኑ ከሰዉ በላዉ ሥርዓት ጋር በመቆም ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የተንበሻበሸች ዓ