Breaking News! ኧረ እሪ የሚያስብል ነው!
የድርቡሽ ሰራዊት ጎንደር እየሰፈረ ነው!
ወያኔ ሙሉ ስምምነት አድርጓል!
ድንበሩን አሳልፈው ሰጥተዋል!
ይህ ፎቶ አርማጭሆ ወረዳ አብደራፊ ላይ ነው የተነሳው። የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር በተመለከተ የወያኔ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች፣ የብአዴን የክልልና የዞኑ ተላላኪ ባለስልጣናት ከሱዳን ወታደራዊ መኮነኖች ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የሱዳን ሰራዊት ድንበር ጥሶ ገብቶ ወያኔ የቸረውን መሬት እየተረከበ ነው። ድንበሩን ለማስከበር የሚዋደቀውንም ገበሬ ከፊት ሱዳን ከኋላ ወያኔ እያጠቁት ነው።
ሆድ አደር የሆኑ የብአዴን ሚሊሻወችን በመሰብሰብ ዳሸን ቢራ በነፃ እያደሉ እርካሽነታቸውን አስመስክረዋል። የምክክር መድረክ በሚል ሰበብ አብደራፊ ለስርአቱ ተገዥ የሆኑ ባለ ሀብቶች የተቀማ መሬታቸውን ከሱዳኖች ተከራይተው እንዲያርሱ ሲያስማሙ ሰንብተዋል። ይህም የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ለሱዳኖች ማበርከት ነው። ሴራው ድንበር እያፈረሰ ነው። ነገር ግን እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ሰፊውን የአብደራፊንና የጠገዴን ህዝብ የማይወክሉ መሆኑን ከቦታው እልህና ቁጭት የገባቸው ወገኖች ሴራውን ከነፎቶ ማስረጃው ልከው አጋልጠዋል። የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በድብቅ እየተሰራ ያለውን መሰሪ የድንበር ማፍረስ ወንጀል ይወቅ ከጎናችንም ይቁም ብለው ጥሪ አስተላልፈዋል።
ከዚህ በላይ አንገብጋቢ ሃገራዊ ጉዳይ የለምና የኢትዮጵያ ህዝብ ተረባርቦ ድንሩረን ያስጠብቅ!
ሙሉነህ ዮሃንስ
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳዮች ኮሚቴ
የቦርድ አባል





Comments

Popular posts from this blog

Addis standard’s exclusive interview with Ana Gomes