የኖርዌይ ኦስሎ እኔ ለነፃነቴ የአንድነት እና የዲሞክራሲ ድጋፍ ዝግጅት የዘመናት ጠላቶችዋን መክታ ሕልውናዋን ጠብቃ መኖር ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ተምሳሌት ሆና ታፍራና ተከብራ የኖረችው ጥንታዊትዋ ሐገራችን ዛሬ በደደቢት በረሐ ከውስጥዋ የበቀሉ የእናት ጡት ነካሾች እንደ ሐገር የመቀጠል ሕልውናዋን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመጣል የሕዝቡን መከራና ስቃይ እስር እና እንግልት በማብዛት አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ ጣሩን ያበዙበት ሕዝባችን ከዳር እስከዳር በቃኝ ፤ሰለቸኝ ብሎ በመነሳት ለነፃነት የሚከፈለውን መስዋትነት ሁሉ እየከፈለ ወያኔን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል። ይህ ዙሪያ ገባውን እንቢ፣በቃኝ፣ሰለቸኝ ብሎ በተነሳ የሕዝብ አመፅ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ፋሺስቱ ወያኔ ከመቃብር አፋፍ ላይ ሆኖም እንኩዋ ከአያት ቅድማያቶቹ የወረሰውን ኢትዮጵያን የማፍረስ ተልዕኮ ተግባራዊ ለማድረግ ሐገር እያቃጠለ ፤ንብረት እያወደመ፣ ኢትዮጵያ ሐገራችንን ዙሪያ ገባዋን እየሸጠ በሕዝብ ላይ አፈናውን አጠናክሮ በቃላት ተዘርዝሮ የማያልቅ ከፍተኛ ግፍና በደል እየፈፀመ ይገኛል። ተፈጥሮ የቸረችውን የመናገርና የመተንፈስ መብቱን ተነፍጎ ለከፍተኛ መከራ፣ስቃይ ፣እንግልት እና ስደት የተዳረገው ሕዝባችን ግን እየታሰረም፣እየተገደለም፣እየተሰቃየም " እምቢ ለሐገሬ ፤ እምቢ ለነፃነቴ " በማለት ባንዳውን ወያኔ አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማብሰር በገንዘብ ለማይተመን ሕይወቱ ሳይሳሳ ...