ሕግን ከሚጥስ ቡድን ሕጋዊ ነገር በመጠየቅ ሕጋዊ ልናስመስለው አንሞክር!!
ኢትዮዽያን ሊያስተዳድር ሳይሆን ኢትዮዽያን ሊያጠፋ ስልጣን ከተቆናጠጠው፤ኢትዮዽያን ኢትዮዽያን ከማይሸት ወያኔ ሕጋዊ
ነገር መጠበቁን ትተን ኢትዮዽያችንን የማዳን የኛው የኢትዮዽያኖች ሐላፊነት ነውና የታሪክ ተወቃሽ ላለመሆን በአንድነት እንነሳ።
የኢትዮዽያን
መሬት እየሸጠ፣ሕዝቡዋን በዘር፣በሐይማኖት እየከፋፈለ፣ታሪኩዋን ለማጥፋት ቀን ከሌት እየሮጠ ከሚሰራ የማፊያ ቡድን በሰላማዊ ሰልፍ
ተቃውሞአችንን ለመግለፅ ፈቃድ ጠይቀን በተልካሻ ምክንያት ፈቃድ ተነፈግን እያልን መጮሁን ትተን በአንድነት በመተባበር ለለውጥ እንነሳ፤ ጣሊያንን
ድል የነሳን ኢትዮዽያውያን ከሊቢያ፣ከቱኒዢያ ከመሳሰሉት ሐገሮች በምንም አናንስም!!
ታሪካችን የተፃፈው በደም እንጅ በውሀ አይደለም!!!!!
ታሪካችን የተፃፈው በደም እንጅ በውሀ አይደለም!!!!!
"እናት አባት ቢሞት ባገር ይለቀሳል፣
እህት ወንድም
ቢሞት ባገር ይለቀሳል፣
ሐገር የሞተ
እንደሁ ወዴት ይደረሳል"።
ሕግን ከሚጥስ
ቡድን ሕጋዊ ነገር በመጠየቅ ሕጋዊ ልናስመስለው አንሞክር!!!
ከየሺሀረግ
በቀለ
Comments
Post a Comment