Posts

Image
አዋጅ አዋጅ !!!……….. ልብ ያለዉ ልብ ይበል ጆሮ ያለዉ ይስማ !! July 13, 2014 | Filed under አማርኛ ዜናና መግለጫ | Posted by admin አዋጅ አዋጅ !!!……….. ልብ ያለዉ ልብ ይበል ጆሮ ያለዉ ይስማ !! የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል የተሰጠ መግለጫ አዋጅ አዋጅ !!! ልብ ያለህ ልብ በል ጆሮ ያለህ ስማ !! የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን መታገት አስመልክቶ አጭር መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል።በመግለጫችን የመን ታጋዩን ልታግት የምትችልበት የጸጉር ስንጣቂ የምታክል ምክንያት እንደሌላት ሊኖራትም እንደማይችል ስለሆነም ታጋዩ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የነጻነት ታጋዩ ለፋሽስቱ የወያኔ ቡድን ተላልፎ ቢሰጥ የመን የማይሰረዝ ታሪካዊ ስህተት የምትሰራ መሆኑን ህዝባዊ ሃይላችንም የበቀል እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳውቀን ወያኔም ምናልባት ትግሉን አስቆማለሁ በሚል የሞኝ ስሌት ያደረገው ከሆነ ድርጊቱ ትግሉን በዕልህ እና በበቀል አጅቦ ከመውሰድ እና ከማፋጠን የዘለለ ትልቁ የሃሳብ አባት አንዳርጋቸው በሃገሪቱ ሰማይ ላይ የለቀቀውን የኢትዮጵያዊነት ጸረ ወያኔ መንፈስ አስሮ አሰቃይቶ፣ገሎ ማስቆም እንደማይችል አሳስበን አስገንዝበን ነበር። መግለጫችን የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ግን የየመን መንግስት እንደሰጋነው ትልቁን የቁርጥ ቀን ልጅ ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን አውቀናል። የተከበርከው የታላቅ ታሪክ ባለቤት የሆንከው የ...