የኦህዴድ/ብልጽግና የጉድ ሀገር
![Image](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEjzj0ZsWR-0PDfqB4T-qqU1Nngy2r2L3UTwA_tzV8YZU8r6dOPtU2ELT00wISpM-4dLQ_AyTgP7ffKV0L4pFa6ZQ9vd-oA2e4mJEw8g9hqvmUdob7A1_d_E59um4TsIDUCyzHiRUAUDZkc/s320/FB_IMG_1593470360209.jpg)
የኦህዴድ ብልጽግና የጉድ ሀገር ሰዉ እየተመረጠ ኮንዶሚኒዮም ቤት በሚሰጥባት ሀገር.."እኛ ምትክ ቤት ሳናገኝ ለምን ጎዳና ላይ ትጥሉናላችሁ በማለት የጠየቁ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በታከለ ኡማ ፖሊስ ተደበደቡ። ..በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በቀድሞ ስሙ ቀበሌ 15 በመባል የሚታወቀው ከሜጋ የኪነ-ጥበብ ማዕከል በስተጀርባ የሚገኙ ኗሪዎችን ትላንት ሰኔ 21/2012 ዓ.ም ለሊት በህገወጡ ከንቲባ ታከለ ኡማ የፖሊስ ሰራዊት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጺባቸው ገለጹ። በአካባቢው ለረጅም አመታት የቆዩ ነዋሪዎች ለሰዎች ኮንዶሚኒዬም ቤት እየተሰጠ ባለበት ወቅት እኛ ምትክ ቤት ሳይሰጠን መኖሪያ ቤታችን አፍርሰን ምን ላይ እንውደቅ ሲሉ የጠይቁ ወገኖች ይህን በማስመልከት ከንቲባዉ ይመጣል እሱን አነጋግሩ በማለት ወደ አንድ አካባቢ ካሰባሰቡን በኃላ በለሌት በርካታ ፖሊስ በማምጣት ድብደባ ተፈጽሞብናል ሲሉ ነዋሪዎቹ አቤቱታቸውን ለባልደራስ ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ህጻናት የያዙ እናቶች ጎዳና ላይ እንደተበተኑ ባልደራስ በቦታው በመገኘት አረጋግጧል። በአሳዛኝ ለቅሶ የሚናገሩት ነዋሪዎቾ የት እንሂድ? ሀገር አጣን ለኛ የሚቆረቆር ጠያቂ ወገን አጣን! ግራ ገባን በዚህ የወረርሽኝ ወቅት ያለ መጠልያ በሃገራችን ቤታችን ፈርሶ መንገድ ላይ ወድቀናል እባካችሁ ድረሱልን በማለት በምሬት ተናግረዋል። አንድ የአካባቢው ነዋሪ በኮየ ፈጬ እና በቦሌ ቡልቡላ ለተለያዩ ግለሰቦች ቤት እየተሰጣቸው እኛ በተወለድንበት ከተማ ያለ ሰብሳቢ መቅረታችን አሳዝኖናል ብለዋል። አንዲት ልጅ የያዘኝ እናት ስሜት በሚነካ መልኩ በለቅሶ ሲገልጹ ብዙዎችን አሳዝናል። የኢትዮጵያ ህዝብ መከራችንን ይመልከትልን ያሉት የቀበሌ 15 ነዋሪዎች ስለፍትህ ያነባሉ። በመጨረሻም በቦታዉ...