Posts
Showing posts from May, 2019
Ethiopia:Ethiopis…’’ኢ/ር ታከለ ኡማ አዲስ አበባን አያውቋትም !’’…የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ወቅታዊ ጉ...
- Get link
- X
- Other Apps
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል(ከኤርሚያስ ለገስ)
- Get link
- X
- Other Apps
(ጀግናችን ኤርሚ ከሕዝብ ጎን ስለቆምክ ክለብ እናመሰግናለን) “ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል!” ተላከ: - ለአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት(ባልደራስ) የከበረ ሰላምታዬ ካላችሁበት ይድረሳችሁ፣ የባለአደራ ምክር ቤት “መንግስታዊ የመሬት ወረራ” እየተፈፀመ መሆኑን በጋዜጣዊ መግለጫችሁ ተመልክቻለሁ። የምክርቤት አባላት የወሰዳችሁትን ጠንካራ አቋም ከልቤ እንደምደግፍ ከወዲሁ ለማሳወቅ እፈልጋለሁ። ይህ እምነቴ የሚመነጨው ተቀጥሬ ከማገለግልበት ኢሳት አቋም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው ሲሆን እንደ አንድ አዲስአበቤ እኔም ያገባኛል ከሚል ስሜት ነው። አዲስ አበባ የአዲስአበቤዎች፣ ከተማነቷ ደግሞ የሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ! እንደ እውነቱ ከሆነ አዲስ አበባ እና አዲስአበቤ ህይወቱን ጭምር መስዋዕት አድርጐ የሚታገልላት ሃይል በማግኘቷም መጠነኛ የህሊና እረፍት አግኝቻለሁ። እርግጥም በተስፋይቱ ከተማ የተስፋ ጭላንጭል እንዲፈነጥቅ በማድረጋችሁ ክብር ይገባችኃል። እናንተ በሰላማዊ ትግል እስከመጨረሻው በፅናት ለመታገል የቆረጣችሁ ብርቅዬ የአዲስ አበባ ፍሬዎችን እንዴት መደገፍና ማገዝ እንዳለብን ከቅርብ ወዳጆቼ ጋር ዘወትር የምናሰላስለው ነው። ወደ መግለጫው ስመለስ የባላደራ ምክር ቤቱ በአንድ በኩል “መንግስታዊ ወረራ” ሊካሄድ እንደሆነ የገለጠበት ምክንያት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን እንደሚያፈርስ መግለፁን ተከትሎ እንደሆነ ከመግለጫው ተከታትያለሁ። በሌላ በኩል የባልደራስ ምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራ መስፋፋት እንደሌለበት የፀና እምነት እንዳላችሁ አመላክታችኃል። በሌላ በኩል ፀሎታችን የባሰ አታምጣ የሚለው ቢሆንም ሰሞኑን ከሚኒስትሮች ምክርቤት የተሰማው የማሻሻያ አዋጅ ከድጡ ወደ ማጡ የሚወስድ...