![Image](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEjPZdPrcpQQ6G8_WFX8GH04yTkljO1Cr9Od59akIQXeUsuedq7QCSvstATTV1I7lMWP__1o2e8kqUTpnwSZfyb8Xt3q70kZbiHg8a6lihlumlbquAj1SZpvDOcQz06i6t2PFGdWtOiUmKs/s400/36364115_1971545496210856_1052180950735126528_o.jpg)
የቦምብ ፍንዳታው የሚመረመረው በስድስት ቡድን በተከፈሉ ባለሙያዎች ነው (ኢሳት ዲሲ--ሰኔ 21/2010) በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 16/2010 በመስቀል አደባባይ የተከሰተውን የቦምብ ፍንዳታ ለመመርመር ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ባለሙያዎች በስድስት ቡድን የተከፈሉ መሆናቸውን ምንጮች ገለጹ። ይህ በእንዲህ እንዳለም ከቦምብ ጥቃቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ከታሰሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር በተጨማሪ ስድስት ኮማንደሮችም በተመሳሳይ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የዋስትና መብት የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዶ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ አዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የለውጥ ጉዞ በመደገፍና ለቅልበሳ የሚንቀሳቀሱትን በማውገዝ በተካሄደው ትዕይንተ ሕዝብ ላይ ሰኔ 16 በፈነዳው ቦምብ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ከ150 በላይ ደግሞ ቆስለዋል። የጥቃት ሙከራውን ተከትሎ ቁጥራቸው 30 ያህል ሰዎች ወዲያውኑ መታሰራቸው የተገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳም መታሰራቸው የተገለጸው እለቱኑ ነበር። ከእሳቸው ጋር 10 ያህል የአዲስ አበባና የፌደራል ፖሊስ ባልደረቦች መታሰራቸው በወቅቱ ቢገለጽም የሌሎቹ ፖሊሶች የስልጣን ደረጃ ግን ሳይጠቀስ ቆይቷል። አሁን ዘግይተው በወጡት መረጃዎች ከረዳት ኮሚሽነሩ በተጨማሪ አምስት ኮማንደሮችና አንድ ረዳት ኮማንደር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል። ተከሳሾቹ በሳምንቱ መጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው ዋስትና የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ከልክሎ ለተጨማሪ ምርመራ በእርስር ቤት እንዲቆዩ ወስኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ይህንን የቦምብ ፍንዳታ ለመመርመር ወደ ኢትዮጵያ የ...