በአርበኞች ግንቦት 7 – ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁበት ተደራጁ!
ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል። በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ። አገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የገነባው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አመራር በዘር የተደራጀ በመሆኑ የሕዝቡን አጠቃላይ ብሶት ደግፎ ሊቆም ይችላል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሠራዊቱ እንደ ተቋም ከተበደለው ሕዝብ ጎን እንዲቆም በመጀመሪያ በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ መካሄድ አለበት።በዚህ አቅጣጫ የሚሠሩ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ሠራዊቱ ዘረኛ ገዢዎቹን አስወግዶ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም፣ አይገባምም። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት በሕዝባዊ አመጽ መታገዝ አለበት የሚለው ሁለገብ የትግል የትግል ስትራቴጂ ተመራጭ እንዲሆን ያደረገው ዋነኛ ምክንያት የሠራዊቱ ዘረኛ አወቃቀር ነው። በመረጥነው የትግል ስትራቴጂ መሠረት በሁለቱም ግንባሮች – ማለትም፣ በሕዝባዊ አመጽ እና በሕዝባዊ እምቢተኝነት ግንባሮች ሥራዎች መሠራት አለባቸው። ሁለገብ የትግል ስትራቴጂ እምንፈልገው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ላይ እንዲያደርሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁለቱም የትግል ስትራቴጂዎች አኳያ መደ...